Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሐዋርያት ሥራ 22:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 አሁንስ ለምን ትዘገያለህ? ተነሣና ስሙን እየጠራህ ተጠመቅ፤ ከኃጢአትህም ታጠብ።’

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ታዲያ፣ አሁን ምን ትጠብቃለህ? ተነሥተህ ስሙን እየጠራህ ተጠመቅ፤ ከኀጢአትህም ታጠብ።’

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ታዲያ፥ አሁን ምን ትጠብቃለህ? ተነሥና የእርሱን ስም በመጥራት ተጠመቅ፤ ከኃጢአትህም ታጠብ።’

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 አሁ​ንም የም​ታ​ደ​ር​ገ​ውን ልን​ገ​ርህ፦ ተነሥ ስሙን እየ​ጠ​ራህ ተጠ​መቅ፤ ከኀ​ጢ​አ​ት​ህም ታጠብ።’

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 አሁንስ ለምን ትዘገያለህ? ተነሣና ስሙን እየጠራህ ተጠመቅ ከኃጢአትህም ታጠብ።

Ver Capítulo Copiar




ሐዋርያት ሥራ 22:16
19 Referencias Cruzadas  

ጴጥሮስም “ንስሐ ግቡ፤ ኀጢአታችሁም ይሰረይ ዘንድ እያንዳንዳችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ፤ የመንፈስ ቅዱስንም ስጦታ ትቀበላላችሁ።


የጌታን ስም የሚጠራም ሁሉ ይድናል።’


ከክፉ ኅሊና ለመንጻት ልባችንን ተረጭተንና ሰውነታችንን በንጹህ ውሃ ታጥበን፥ በቅን ልብ በፍጹም እምነት እንቅረብ፤


እኛ በጽድቅ በሠራናቸው ሥራዎች ሳይሆን እንደ ምሕረቱ መጠን ለአዲስ ልደት በሚሆነው መታጠብና በመንፈስ ቅዱስ በመታደስ እኛን አዳነን፤


ከእናንተም አንዳንዶቹ እንደ እነዚህ ነበራችሁ፤ ነገር ግን በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም በአምላካችንም መንፈስ ታጥባችኋል፤ ተቀድሳችኋል፤ ጸድቃችኋል።


ይህ ውሃ አሁን የጥምቀት ምሳሌ ሆኖ እናንተን ያድናል፤ የሰውነትን እድፍ ማስወገድ ሳይሆን፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ፥ ለእግዚአብሔር የሚቀርብ የበጎ ሕሊና ልመና ነው።


ከክርስቶስ ጋር አንድ ለመሆን የተጠመቃችሁ ሁሉ ክርስቶስን ለብሳችሁታል።


አይሁድ ብንሆን የግሪክ ሰዎችም ብንሆን ባርያዎችም ብንሆን ጨዋዎችም ብንሆን እኛ ሁላችን በአንድ መንፈስ አንድ አካል እንድንሆን ተጠምቀናልና። ሁላችንም አንዱን መንፈስ ጠጥተናል።


ትእዛዝህን ለመጠበቅ ጨከንሁ አልዘገየሁምም።


በዚህም ስምህን የሚጠሩትን ሁሉ ለማሰር ከካህናት አለቆች ሥልጣን አለው፤” አለ።


በቆሮንቶስ ላለች ለእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን፥ በክርስቶስ ኢየሱስ ለተቀደሱት፥ ቅዱሳን ለመሆን ለተጠሩት፥ የእነርሱና የእኛ ጌታ የሆነውን የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ስም በየስፍራው ከሚጠሩት ሁሉ ጋር፤


ወዲያውም እንደ ቅርፊት ያለ ከዐይኑ ወደቀ፤ ያን ጊዜም ደግሞ አየ፤ ተነሥቶም ተጠመቀ፤


ዝም ብለን ለምን እንቀመጣለን? ጌታን ስለ በደልን አምላካችን ጌታ አጥፍቶናልና፥ የሐሞትንም ውኃ አጠጥቶናልና ተሰብሰቡ ወደ ተመሸጉ ከተሞች እንግባ በዚያም እንጥፋ።


ወደ ቤርሳቤህ ከገባ በኋላ ነቢዩ ናታን ወደ እርሱ በመጣ ጊዜ፥


ጴጥሮስም “የእኔን እግር በጭራሽ አታጥብም” አለው። ኢየሱስም “ካላጠብሁህ፥ ከእኔ ድርሻ የለህም፤” ብሎ መለሰለት።


እስጢፋኖስም “ጌታ ኢየሱስ ሆይ! ነፍሴን ተቀበል፤” ብሎ ሲጠራ ይወግሩት ነበር።


ከውሃ መታጠብ ጋር በቃሉ አንጽቶ እንዲቀድሳት፥


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios