ይህንንም የማደርገው ሰሎሞን እኔን ትቶ ባዕዳን የሆኑትን ዐስታሮት ተብላ የምትጠራውን የሲዶና አምላክ፥ ኬሞሽ ተብሎ የሚጠራውን የሞዓብ አምላክና ሚልኮም ተብሎ የሚጠራውን የዐሞን አምላክ ስላመለከ ነው፤ ሰሎሞን ለእኔ ታዛዥ አልሆነም፤ እርሱ አባቱ ዳዊት ለእኔ ይታዘዝ እንደ ነበር ሕጎቼንና ትእዛዞቼን ባለመጠበቁ በድሎአል።
መሳፍንት 10:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እስራኤላውያን እንደገና በጌታ ላይ ክፉ ድርጊት ፈጸሙ፤ በኣልንና አስታሮትን እንዲሁም የሶሪያን፥ የሲዶናን፥ የሞዓብን፥ የአሞንንና የፍልስጥኤማውያንን አማልክት አመለኩ፤ እስራኤላውያን ጌታን ስለተዉና ስላላገለገሉት፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስራኤላውያን እንደ ገና በእግዚአብሔር ላይ ክፉ ድርጊት ፈጸሙ፤ በኣልንና አስታሮትን እንዲሁም የአራምን፣ የሲዶናን፣ የሞዓብን፣ የአሞንንና የፍልስጥኤማውያንን አማልክት አመለኩ፤ እስራኤላውያን እግዚአብሔርን ስለ ተዉና ስላላገለገሉት፣ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እስራኤላውያን ባዓልና ዐስታሮት የተባሉትን ባዕዳን አማልክት እንዲሁም የሶርያን፥ የሲዶናን፥ የሞአብን፥ የዐሞንንና የፍልስጥኤምን አማልክት በማምለክ እንደገና እግዚአብሔርን በደሉ፤ እርሱንም ማምለክ ተዉ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእስራኤልም ልጆች በእግዚአብሔር ፊት እንደ ገና ክፉ ሥራ ሠሩ፤ በዓሊምንና አስታሮትን፥ የሶርያንም አማልክት፥ የሲዶናንም አማልክት፥ የሞዓብንም አማልክት፥ የአሞንንም ልጆች አማልክት፥ የፍልስጥኤማውያንንም አማልክት አመለኩ፤ እግዚአብሔርንም ተዉ፤ አላመለኩትምም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስራኤልም ልጆች በእግዚአብሔር ፊት እንደ ገና ክፉ ሥራ ሠሩ በኣሊምንና አስታሮትን የሶርያንም አማልክት፥ የሲዶናንም አማልክት፥ የሞዓብንም አማልክት፥ የአሞንንም ልጆች አማልክት፥ የፍልስጥኤማውያንንም አማልክት አመለኩ፥ እግዚአብሔርንም ተዉ፥ አላመለኩትምም። |
ይህንንም የማደርገው ሰሎሞን እኔን ትቶ ባዕዳን የሆኑትን ዐስታሮት ተብላ የምትጠራውን የሲዶና አምላክ፥ ኬሞሽ ተብሎ የሚጠራውን የሞዓብ አምላክና ሚልኮም ተብሎ የሚጠራውን የዐሞን አምላክ ስላመለከ ነው፤ ሰሎሞን ለእኔ ታዛዥ አልሆነም፤ እርሱ አባቱ ዳዊት ለእኔ ይታዘዝ እንደ ነበር ሕጎቼንና ትእዛዞቼን ባለመጠበቁ በድሎአል።
ከኢየሩሳሌም በስተ ምሥራቅ በሚገኘው ተራራ ላይ አጸያፊዎች ለሆኑት ኬሞሽ ተብሎ ለሚጠራው ለሞአባውያን አምላክና ሞሌክ ተብሎ ለሚጠራው ለዐሞናውያን አምላክ የመስገጃ ስፍራዎችን አዘጋጀላቸው።
አክዓብ፥ ንጉሥ ኢዮርብዓም የሠራውን ኃጢአት እንደ ቀላል ነገር አድርጎ በመቁጠር እርሱም ራሱ ያንኑ ኃጢአት ሠራ፤ ከዚህም ሁሉ አልፎ የሲዶና ንጉሥ የኤትበዓል ልጅ የሆነችውን አረማዊቷን ኤልዛቤልን አገባ፤ ባዓል ተብሎ የሚጠራውንም ጣዖት አመለከ፤ ሰገደለትም።
የአምላካቸውን የእግዚአብሔርን ትእዛዞች ሁሉ በመጣስ የሚሰግዱላቸውን ከወርቅ የተሠሩ ሁለት ጥጆችን አቆሙ፤ እንዲሁም አሼራ ተብላ የምትጠራውን ሴት አምላክ ምስል ሠሩ፤ ለከዋክብት ሰገዱ፤ በዓል ተብሎ ለሚጠራውም ባዕድ አምላክ አገልጋዮች ሆኑ።
እንዲሁም ከኢየሩሳሌም በስተ ምሥራቅ ከርኲሰት ተራራ በስተ ደቡብ ዐስታሮት ተብላ ለምትጠራው ለሲዶና አምላክ፥ ከሞሽ ተብሎ ለሚጠራው ለሞዓብ አምላክና ሞሌክ ተብሎ ለሚጠራው ለዐሞን አምላክ ንጉሥ ሰሎሞን አሠርቶአቸው የነበሩት አጸያፊዎች ምስሎች ሁሉ የረከሱ መሆናቸውን አስገነዘበ።
ድል ለነሡትም ለደማስቆ አማልክት፦ “የሶሪያን ነገሥታት አማልክት ረድተዋቸዋልና እኔን እንዲረዱኝ እሠዋላቸዋለሁ” ብሎ ሠዋላቸው። ነገር ግን ለእርሱና ለእስራኤል ሁሉ እንቅፋት ሆኑ።
ሕዝቤ ሁለት ክፉ ነገሮችን ሠርቷል፤ እኔን የሕይወት ውኃ ምንጭን ትተውኛል፥ ውኃ መቋጠር የማይችሉ የተሸነቈሩ ጉድጓዶች ለራሳቸው ቆፍረዋል።
“ከጥንት ጀምሮ ቀንበርሽን ሰብረሻል እስራትሽንም በጥሰሻል፤ አንቺም፦ ‘አላገለግልም’ አልሽ፥ ነገር ግን ከፍ ባለው ኮረብታ ሁሉ ላይ ከለምለምም ዛፍ ሁሉ በታች ለማመንዘር ተጋደምሽ።
እነርሱም ገብተው ወረሱአት፤ ነገር ግን ድምፅህን አልሰሙም በሕግህም አልሄዱም፥ እንዲያደርጉም ካዘዝሃቸው ሁሉ ምንም አላደረጉም፤ ስለዚህ ይህን ክፉ ነገር ሁሉ አመጣህባቸው።
ከምርትሽ ብዛት የተነሣ አራም ነጋዴሽ ነበረች፤ ዕቃዎችሽን በበሉር፥ በወይን ጠጅ፥ በወርቀ ዘቦ፥ በጥሩ በፍታም በዛጐልም በቀይ ዕንቁም ይቀይሩ ነበር።
“የአባትህ፥ ወይም የእናትህ ልጅ ወንድምህ፥ ወንድ ልጅህ፥ ወይም ሴት ልጅህ ወይም የምትወዳት ሚስትህ ወይም የቅርብ ወዳጅህ አንዳቸው ቢሆኑ በምሥጢር ሊያስትህ ቢሞክር፥
ጌታም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “እነሆ፥ ከአባቶችህ ጋር ልታርፍ ነው፤ ይህም ሕዝብ በሚገባበት ምድር በሚገኙ ባዕዳን አማልክት ወዲያውኑ ያመነዝራል። እኔን ይተወኛል፤ ከእነርሱም ጋር የገባሁትን ኪዳን ያፈርሳሉ።
በዚያች ቀን እቀጣቸዋለሁ፤ እተዋቸዋለሁም፤ ፊቴን ከእነርሱ እሰውራለሁ፤ እነርሱም ይጠፋሉ። ብዙ ጥፋትና የከፋ ችግር ይደርስባቸዋል፤ በዚያችም ቀን፥ ‘ይህ ጥፋት የደረሰብን፥ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ባለመሆኑ አይደለምን?’ ይላሉ።
የገለዓድም እኩሌታ፥ በባሳንም ያሉት የዐግ መንግሥት ከተሞች፥ አስታሮትና ኤድራይ ነበረ። እነዚህም ለማኪር ልጆች እኩሌታ በየወገኖቻቸው ለምናሴ ልጅ ለማኪር ልጆች ድርሻቸው ሆነ።
አምላክህ ካሞሽ የሰጠህን ይዞ ማቈየቱ ያንተ ፈንታ አይደለምን? እኛስ እንደዚሁ አምላካችን ጌታ የሰጠንን ሁሉ ርስት አድርገን ልንወርስ አይገባንምን?
በዚህ ጊዜ የፍልስጥኤማውያን ገዦች፥ “አምላካችን ዳጎን፥ ጠላታችን ሳምሶንን በእጃችን አሳልፎ ሰጥቶናል” ብለው በመደሰት ለአምላካቸው ለዳጎን ታላቅ መሥዋዕት ለማቅረብ ተሰበሰቡ።