La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢያሱ 15:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ድንበሩም በሄኖም ልጅ ሸለቆ አጠገብ ኢየሩሳሌም ወደምትባለው ወደ ኢያቡሳዊው ወደ ደቡብ ወገን ወጣ፤ ድንበሩም በራፋይም ሸለቆ ዳር በሰሜን በኩል ባለው በሄኖም ሸለቆ ፊት ለፊት በምዕራብ ወገን ወዳለው ተራራ ራስ ላይ ወጣ፤

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እንደዚሁም የሄኖምን ልጅ ሸለቆ ዐልፎ ይሄድና የኢያቡሳውያን ከተማ እስከ ሆነችው እስከ ኢየሩሳሌም ደቡባዊ ተረተር በመዝለቅ፣ በራፋይም ሸለቆ ሰሜን ጫፍ በኩል አድርጎ ከሄኖም ሸለቆ በስተ ምዕራብ ካለው ኰረብታ ዐናት ላይ ይደርሳል።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ድንበሩ በሔኖም ልጅ ሸለቆ ከደቡብ ዝቅተኛ ቦታ የኢያቡሳውያን ከተማ በሆነችው በኢየሩሳሌም በኩል ከሔኖም ሸለቆ ፊት ለፊት እስካለው ተራራ ጫፍ ድረስ በመዝለቅ በሰሜን በኩል ወደ ሬፋይም ሸለቆ ይደርሳል።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ድን​በ​ሩም በሄ​ኖም ልጅ ሸለቆ አጠ​ገብ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ወደ​ም​ት​ባ​ለው ወደ ኢያ​ቡስ ወደ ደቡብ ወገን ይወ​ጣል፤ ድን​በ​ሩም በሰ​ሜን በኩል በራ​ፋ​ይም ሸለቆ ዳር ባለው በሄ​ኖም ሸለቆ ፊት ለፊት በባ​ሕር በኩል ወዳ​ለው ተራራ ራስ ላይ ይወ​ጣል፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ድንበሩም በሄኖም ልጅ ሸለቆ አጠገብ ኢየሩሳሌም ወደምትባለው ወደ ኢያቡሳዊው ወደ ደቡብ ወገን ወጣ፥ ድንበሩም በራፋይም ሸለቆ ዳር በሰሜን በኩል ባለው በሄኖም ሸለቆ ፊት ለፊት በምዕራብ ወገን ወዳለው ተራራ ራስ ላይ ወጣ፥

Ver Capítulo



ኢያሱ 15:8
17 Referencias Cruzadas  

ፍልስጥኤማውያንም መጥተው በራፋይም ሸለቆ ተበታትነው ሰፈሩ።


ፍልስጥኤማውያን እንደገና መጥተው በራፋይም ሸለቆ ተበታትነው ሰፈሩ።


ንጉሥ ኢዮስያስ በሒኖም ሸለቆ የነበረው “ቶፌት” ተብሎ የሚጠራው የአሕዛብ ማምለኪያ ቦታ የረከሰ መሆኑን አስገነዘበ፤ ከዚህም የተነሣ “ሞሌክ” ተብሎ ለሚጠራው አምላክ ወንድ ልጁን ወይም ሴት ልጁን መሥዋዕት አድርጎ የሚያቀርብ ማንም እንዳይኖር ተከለከለ፤


ዳዊትም እስራኤልም ሁሉ ኢያቡስ ወደምትባል ወደ ኢየሩሳሌም ሄዱ፤ በአገሩም የተቀመጡ ኢያቡሳውያን በዚያ ነበሩ።


ደግሞም በሄኖም ልጅ ሸለቆ ውስጥ ዐጠነ፤ ጌታ ከእስራኤል ልጆች ፊት እንዳሳደዳቸው እንደ አሕዛብም ክፉ ልማድ ልጆቹን በእሳት አቃጠለ።


ዛኖሓ፥ ዓዱላምና በመንደሮቻቸው፥ ላኪሽና ሜዳዎችዋ፥ ዓዚቃና በመንደሮችዋ፤ እንዲሁ ከቤርሳቤህ ጀምሮ እስከ ሄኖም ሸለቆ ድረስ ሰፈሩ።


አጫጅ የቆመውን እህል በእጁ ሰብስቦ ዛላውን እንደሚያጭድ፥ በራፋይም ሸለቆ እንደሚለቀም ቃርሚያ ይሆናል።


ኤርምያስም ጌታ ትንቢት እንዲናገር ልኮት ከነበረበት ስፍራ ከቶፌት መጣ፥ በጌታም ቤት አደባባይ ቆሞ ለሕዝብ ሁሉ እንዲህ አለ፦


በካርሲት በር መግቢያ አጠገብ ወዳለው ወደ ሄኖም ልጅ ሸለቆ ሂድ፥ በዚያም የምነግርህን ቃላት ተናገር፥


ስለዚህ፥ እነሆ፥ ይህ ስፍራ የእርድ ሸለቆ ይባላል እንጂ ቶፌት ወይም የሄኖም ልጅ ሸለቆ ዳግመኛ የማይባልበት ዘመን ይመጣል፥ ይላል ጌታ።


በኢየሩሳሌም የተቀመጡትን ኢያቡሳውያንን ግን የይሁዳ ልጆች ሊያሳድዱአቸው አልቻሉም፤ ኢያቡሳውያንም እስከ ዛሬ በይሁዳ ልጆች መካከል በኢየሩሳሌም ውስጥ ተቀምጠዋል።


ድንበሩም በሄኖም ልጅ ሸለቆ ፊት ለፊት ወዳለው ተራራ መጨረሻ ወረደ፥ እርሱም በራፋይም ሸለቆ በሰሜን በኩል ነው፤ ወደ ሄኖም ሸለቆ ወደ ኢያቡስ ወገን በደቡብ በኩል ወረደ፥ ወደ ዓይንሮጌልም ወረደ።


ጼላ፥ ኤሌፍ፥ ኢየሩሳሌም የምትባል ኢያቡስ፥ ጊብዓና ቂርያትይዓሪም፤ ዐሥራ ሦስት ከተሞችና መንደሮቻቸው። የብንያም ልጆች ርስት በየወገኖቻቸው ይህ ነበረ።


ነገር ግን የብንያም ሰዎች በኢየሩሳሌም የሚኖሩትን ኢያቡሳውያንን ከዚያ አላስወጧቸውም፤ ስለዚህ ኢያቡሳውያን እስከ ዛሬ ድረስ ከብንያማውያን ጋር በዚያ አብረው ይኖራሉ።


የይሁዳ ሰዎች ኢየሩሳሌምን ወግተው ያዟት፤ ከተማይቱንም በሰይፍ ስለት መተው፥ በእሳት አቃጠሏት።


ሌዋዊው ግን በዚያች ሌሊት በዚያ ለማደር ስላልፈለገ ተነሥቶ የተጫኑትን ሁለቱን አህዮቹንና ቁባቱን ይዞ ኢየሩሳሌም ወደተባለችው ወደ የቡስ ሄደ።