Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -


ኢያሱ 15 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም


ለይሁዳ ነገድ የተመደበው ድርሻ
15፥15-19 ተጓ ምብ – መሳ 1፥11-15

1 ለይሁዳ ነገድ በየጐሣቸው በዕጣ የተመደበው ድርሻ እስከ ኤዶም ምድር የሚወርድ ሲሆን፣ በስተ ደቡብ መጨረሻ እስከ ጺን ምድረ በዳ ድረስ ይዘልቃል።

2 የደቡብ ወሰናቸው፣ ከጨው ባሕር ደቡባዊ ጫፍ ካለው የባሕር ወሽመጥ ይነሣል፤

3 ከዚያም የአቅረቢምን መተላለፊያ በማቋረጥ በጺን በኩል እስከ ቃዴስ በርኔ ደቡባዊ ክፍል ይደርሳል፤ ደግሞም ሐጽሮንን ዐልፎ ወደ አዳር ይወጣና ወደ ቀርቃ ይታጠፋል፤

4 በዓጽሞን በኩል አድርጎም ወደ ግብጽ ደረቅ ወንዝ ይገባና መቆሚያው ባሕሩ ይሆናል። እንግዲህ በደቡብ በኩል ያለው ወሰናቸው ይህ ነው።

5 በምሥራቅ በኩል ያለው ወሰናቸው ደግሞ የጨው ባሕር ሲሆን፣ ይህም የዮርዳኖስ ወንዝ እስከሚሠርግበት ይደርሳል። በሰሜን በኩል ያለው ወሰንም የዮርዳኖስ ወንዝ ከሚሠርግበት የባሕር ወሽመጥ ይነሣና

6 ሽቅብ ወደ ቤትሖግላ ይወጣል፤ ከዚያም በሰሜናዊው ቤትዓረባ በኩል አድርጎ የሮቤል ልጅ የቦሀን ድንጋይ እስካለበት ይደርሳል።

7 ከዚያም ድንበሩ ከአኮር ሸለቆ ወደ ዳቤር ይወጣና ከወንዙ በስተ ደቡብ ባለው በአዱሚም መተላለፊያ ፊት ለፊት አድርጎ በስተሰሜን ወደ ጌልገላ ይታጠፋል፤ በዓይንሳሚስ ምንጭ በኩል ዐልፎም ወደ ዓይንሮጌል ይወጣል።

8 እንደዚሁም የሄኖምን ልጅ ሸለቆ ዐልፎ ይሄድና የኢያቡሳውያን ከተማ እስከ ሆነችው እስከ ኢየሩሳሌም ደቡባዊ ተረተር በመዝለቅ፣ በራፋይም ሸለቆ ሰሜን ጫፍ በኩል አድርጎ ከሄኖም ሸለቆ በስተ ምዕራብ ካለው ኰረብታ ዐናት ላይ ይደርሳል።

9 ከዚያም በመቀጠል ከተራራው ዐናት ተነሥቶ ወደ ኔፍቶ ምንጮች በማምራት፣ በዔፍሮን ተራራ ላይ ያሉትን ከተሞች ዐልፎ ይወጣና ቂርያትይዓይሪም ተብሎ ወደሚጠራው ወደ በኣላ ቍልቍል ይወርዳል።

10 ከዚያም ከበኣላ በምዕራብ በኩል አድርጎ ወደ ሴይር ይታጠፍና ክሳሎን ተብሎ በሚጠራው በይዓሪም ኰረብታ ሰሜናዊ ተረተር ዐልፎ ቍልቍል ወደ ቤትሳሚስ በመውረድ ወደ ተምና ይሻገራል።

11 ደግሞም በአቃሮን ሰሜናዊ ተረተር አድርጎ ወደ ሽክሮን ይታጠፍና በበኣላ ተራራ ላይ ዐልፎ እስከ የብኒኤል ይደርሳል፤ ከዚህ በኋላ ወሰኑ ባሕሩ ላይ ይቆማል።

12 የምድሪቱ ምዕራባዊ ወሰን የታላቁ ባሕር ጠረፍ ነው። እንግዲህ በየጐሣው የተደለደለውን የይሁዳን ሕዝብ በዙሪያው የከበቡት ወሰኖቹ እነዚሁ ናቸው።

13 ኢያሱ እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት፣ ከይሁዳ ድርሻ ላይ ከፍሎ ኬብሮን የተባለችውን ቂርያት አርባቅን ለዮፎኒ ልጅ ለካሌብ ሰጠው፤ አርባቅም የዔናቅ አባት ነበረ።

14 ካሌብም ሦስቱን የዔናቅን ዘሮች ሴሲንን፣ አኪመንንና ተላሚንን ከኬብሮን አሳደዳቸው፤

15 ከዚያም በዳቤር ሕዝብ ላይ ዘመተ፤ ዳቤር ቀድሞ ቂርያትሤፍር ትባል ነበር።

16 ካሌብ፣ “ቂርያትሤፍርን ወግቶ ለሚይዝ ሰው ልጄን ዓክሳን እድርለታለሁ” አለ።

17 ስለዚህ የካሌብ ወንድም የቄኔዝ ልጅ ጎቶንያል ከተማዪቱን ያዛት፤ ካሌብም ልጁን ዓክሳን ዳረለት።

18 ዓክሳ ወደ ጎቶንያል በመጣች ጊዜም፣ ከአባቷ ላይ የዕርሻ መሬት እንዲለምን አጥብቃ ነገረችው። ከአህያዋ ላይ እንደ ወረደች ካሌብ፣ “ምን እንዳደርግልሽ ትፈልጊያለሽ?” ሲል ጠየቃት።

19 እርሷም፣ “እባክህ፤ ባርከኝ፤ በኔጌብ መሬት እንደ ሰጠኸኝ ሁሉ፣ አሁንም የውሃ ምንጭ ጕድጓዶች ስጠኝ” አለችው፤ ካሌብም የላይኛውንና የታችኛውን ምንጮች ሰጣት።

20 ለይሁዳ ነገድ በየጐሣቸው የተሰጣቸው ርስት ይህ ነው፤

21 በኔጌብ አካባቢ በኤዶም ድንበር ላይ በወሰኑ ጫፍ የሚገኙት የይሁዳ ነገድ ደቡባዊ ከተሞች እነዚህ ነበሩ፤ ቀብጽኤል፣ ዔዴር፣ ያጉር፣

22 ቂና፣ ዲሞና፣ ዓድዓዳ፣

23 ቃዴስ፣ ሐጾር፤ ዩትናን፣

24 ዚፍ፣ ጤሌም፣ በዓሎት፣

25 ሐጾርሐዳታ፣ ሐጾር የምትባለው ቂርያትሐጾር

26 አማም፣ ሽማዕ፣ ሞላዳ፣

27 ሐጻርጋዳ፣ ሐሽሞን፣ ቤትጳሌጥ፣

28 ሐጻርሹዓል፣ ቤርሳቤህ፣ ቢዝዮትያ

29 በኣላ፣ ዒዪም፣ ዔጼም፣

30 ኤልቶላድ፣ ኪሲል፣ ሖርማ፣

31 ጺቅላግ፣ ማድማና፣ ሳንሳና

32 ልባዎት፣ ሺልሂም፣ ዓይንና ሪሞን ናቸው፤ በአጠቃላይም ከተሞቹና መንደሮቻቸው ሃያ ዘጠኝ ናቸው።

33 በምዕራቡ በኰረብታዎች ግርጌ ያሉት ደግሞ እነዚህ ናቸው፤ ኤሽታኦል፤ ጾርዓ፣ አሽና

34 ዛኖዋ፣ ዓይንገኒም፣ ታጱዋ፣ ዓይናም፣

35 ያርሙት፣ ዓዶላም፣ ሦኮን፣ ዓዜቃ፣

36 ሽዓራይም፣ ዓዲታይም፣ ግዴራ፣ ግዴሮታይም ናቸው፤ ከተሞቹም ከነመንደሮቻቸው ዐሥራ አራት ናቸው።

37 ጽናን፣ ሐዳሻ፣ ሚግዳልጋድ፣

38 ዲልዓን፣ ምጽጳ፣ ዮቅትኤል፣

39 ለኪሶ፣ ቦጽቃት፣ ዔግሎን፣

40 ከቦን፣ ለሕማስ፣ ኪትሊሽ፣

41 ግዴሮት፣ ቤትዳጎን፣ ናዕማና መቄዳ ናቸው፤ ከተሞቹም ከነመንደሮቻቸው ዐሥራ ስድስት ናቸው።

42 ልብና፣ ዔቴር፣ ዓሻን

43 ይፍታሕ፣ አሽና፣ ንጺብ፣

44 ቅዒላ፣ አክዚብና መሪሳ ናቸው፤ ከተሞቹም ከነመንደሮቻቸው ዘጠኝ ናቸው።

45 አቃሮን በዙሪያዋ ካሉ ሰፈሮችና መንደሮቿ ጋራ፣

46 እንዲሁም ከአቃሮን በስተ ምዕራብ በአሽዶድ አካባቢ ያሉ ሰፈሮችና መንደሮቻቸው ሁሉ፣

47 አሽዶድ በዙሪያዋ ካሉ ሰፈሮችና መንደሮች ጋራ፣ ጋዛ እስከ ግብጽ ደረቅ ወንዝና እስከ ታላቁ ባሕር ጠረፍ በመለስ ካሉት ሰፈሮቿና መንደሮቿ ጋራ።

48 በኰረብታማዋም አገር የሚገኙ ከተሞች ደግሞ እነዚህ ናቸው፤ ሳምር፣ የቲር፣ ሶኮ

49 ደና፣ ዳቤር የምትባለው ቂርያትስና

50 ዓናብ፣ ኤሽትሞዓ፣ ዓኒም፣

51 ጎሶም፣ ሖሎንና ጊሎ፤ እነዚህም ዐሥራ አንዱ ከተሞችና መንደሮቻቸው ናቸው።

52 አራብ፣ ዱማ፣ ኤሽዓን፣

53 ያኒም፣ ቤትታጱዋ፣ አፌቃ

54 ሑምጣ፣ ኬብሮን የተባለችው ቂርያት አርባቅና ጺዖር ናቸው፤ እነዚህም ዘጠኝ ከተሞችና መንደሮቻቸው ናቸው።

55 ማዖን፣ ቀርሜሎስ፣ ዚፍ፣ ዩጣ

56 ኢይዝራኤል፣ ዮቅድዓም፣ ዛኖዋሕ፣

57 ቃይን፣ ጊብዓና ተምና ናቸው፤ እነዚህም ዐሥር ከተሞችና መንደሮቻቸው ናቸው።

58 ሐልሑል፣ ቤትጹር፣ ጌዶር፣

59 ማዕራት፣ ቤትዓኖትና ኤልትቆን ናቸው፤ እነዚህም ስድስት ከተሞችና መንደሮቻቸው ናቸው።

60 ቂርያትይዓይሪም የተባለችው ቂርያትበኣልና ረባት፤ እነዚህም ሁለት ከተሞችና መንደሮቻቸው ናቸው።

61 በምድረ በዳው ደግሞ እነዚህ ናቸው፤ ቤትዓረባ፣ ሚዲን፣ ስካካ፣

62 ኒብሻን፣ የጨው ከተማና ዓይንጋዲ፤ እነዚህም ስድስት ከተሞችና መንደሮቻቸው ናቸው።

63 ነገር ግን የይሁዳ ዘሮች በኢየሩሳሌም የሚኖሩትን ኢያቡሳውያን ከቦታቸው ሊያስለቅቋቸው አልቻሉም፤ ኢያቡሳውያንም እስከ ዛሬ ድረስ ከይሁዳ ሕዝብ ጋራ በኢየሩሳሌም ዐብረው ይኖራሉ።

መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™

የቅጂ መብት © 2001, 2024 በBiblica, Inc.

በፈቃድ የሚወሰድ። በዓለም ዐቀፍ ባለቤትነቱ።

The Holy Bible, New Amharic Standard Version™

Copyright © 2001, 2024 by Biblica, Inc.

Used with permission. All rights reserved worldwide. 

Biblica, Inc.
Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos