ዮናስ 1:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ተነሥ፥ ወደ ታላቂቱ ከተማ ወደ ነነዌ ሂድ፥ በእርሷ ላይ ስበክ፤ ክፋታቸው በፊቴ ወጥቶአልና።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ወደ ታላቂቱ ከተማ ወደ ነነዌ ሄደህ፣ በርሷ ላይ ስበክ፤ ክፋቷ በእኔ ፊት ወጥቷልና።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ተነሥተህ ወደ ታላቂቱ ከተማ ወደ ነነዌ ሂድ፤ እኔ የሕዝብዋን ክፋት ተመልክቼአለሁ። ድምፅህንም ከፍ አድርገህ እርስዋን በመገሠጽ ተናገር።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ተነሥተህ ወደ ታላቂቱ ከተማ ወደ ነነዌ ሂድ፤ የክፋታቸውም ጩኸት ወደ ፊቴ ወጥቶአልና ለእነርሱ ስበክ።” |
በዚያም ዖዴድ የተባለ የጌታ ነቢይ ነበረ፤ ወደ ሰማርያም የሚመጣውን ጭፍራ ሊገናኘው ወጣ፥ እንዲህም አላቸው፦ “እነሆ፥ የአባቶቻችሁ አምላክ ጌታ ይሁዳን ስለ ተቈጣ በእጃችሁ አሳልፎ ሰጣቸው፥ እናንተም ወደ ሰማይ በሚደርስ ቁጣ ገደላችኋቸው።
እንዲህም አልሁ፦ “አምላኬ ሆይ፥ አፍሬአለሁ፤ አምላኬ ሆይ፥ ፊቴንም ወደ አንተ ለማንሣት እፈራለሁ፥ ኃጢአታችን ከራሳችን በላይ ከፍ ብሏልና፥ በደላችንም ወደ ሰማያት ወጥቷልና።
እኔም፦ “የጌታን ስም አላነሣም፥ ከእንግዲህ ወዲህም በስሙ አልናገርም” ብል፥ በአጥንቶቼ ውስጥ እንደ ገባ እንደሚነድድ እሳት ያለ በልቤ ሆነብኝ፤ ደከምሁ፥ መሸከምም አልቻልሁም።
ስብራትህን የሚያሽል የለም፥ ቁስልህ የከፋ ነው፤ ወሬህን የሰሙ ሁሉ እጃቸውን በአንተ ላይ ያጨበጭባሉ፤ የማያቋርጥ ክፋትህ ያላለፈበት ማን ነውና?
የነነዌ ሰዎች በፍርድ ቀን ከዚህ ትውልድ ጋር ተነሥተው ይፈርዱበታል፤ በዮናስ ስብከት ንስሐ ገብተዋልና፤ እነሆ ከዮናስ የሚበልጥ እዚህ አለ።