ናሆም 3:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)19 ስብራትህን የሚያሽል የለም፥ ቁስልህ የከፋ ነው፤ ወሬህን የሰሙ ሁሉ እጃቸውን በአንተ ላይ ያጨበጭባሉ፤ የማያቋርጥ ክፋትህ ያላለፈበት ማን ነውና? Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም19 ቍስልህን ሊፈውስ የሚችል የለም፤ ስብራትህም ለሞት የሚያደርስ ነው። ስለ አንተ የሰማ ሁሉ፣ በውድቀትህ ደስ ብሎት ያጨበጭባል፤ ወሰን የሌለው ጭካኔህ ያልነካው ማን አለና? Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም19 ክፉኛ የተጐዳሽ ስለ ሆነ ቊስልሽን ሊፈውስ የሚችል ነገር የለም፤ ማለቂያ ከሌለው ከአንቺ የጭካኔ ድርጊት ያመለጠ ሰው ስለሌለ ስለ አንቺ የሚሰሙ ሁሉ በአንቺ መውደቅ ያጨበጭባሉ። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)19 ስብራትህ አይፈወስም፥ ቁስልህም ክፉ ነው፣ ወሬህንም የሚሰሙ ሁሉ እጃቸውን በአንተ ላይ ያጨበጭባሉ፣ ክፋትህ ሁልጊዜ ያላለፈችበት ሰው ማን ነውና? Ver Capítulo |