ኢዮብ 31:35 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሚያዳምጠኝ ምነው በኖረልኝ! እነሆ የእጄ ምልክት፥ ሁሉን የሚችል አምላክ ይመልስልኝ፥ ከባላጋራዬ የተጻፈው የክስ ጽሑፍ ምነው በተገኘልኝ! አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ምነው የሚሰማኝ ባገኝ! የመከላከያ ፊርማዬ እነሆ፤ ሁሉን ቻይ አምላክ ይመልስልኝ፤ ከሳሼም ክሱን በጽሑፍ ያቅርብ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ምነው የሚሰማኝ ባገኘሁ! መከላከያዬን አቀርባለሁ፤ ሁሉን ቻይ አምላክ ይመልስልኝ! ምነው ከሳሼም የክሱን ዝርዝር በጽሑፍ አቅርቦልኝ ባየሁት! የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሚያደምጠኝን ማን በሰጠኝ! የእግዚአብሔርንም እጅ አልፈራሁ እንደ ሆነ፥ የሚያስፈርድብኝ የክስ ጽሑፍ ምነው በኖረኝ! መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሚያዳምጠኝ ምነው በኖረልኝ! እነሆ የእጄ ምልክት፥ ሁሉን የሚችል አምላክ ይመልስልኝ፥ ከባላጋራዬ የተጻፈው የክስ ጽሑፍ ምነው በተገኘልኝ! |
ባላጋራህ ለዳኛ፥ ዳኛውም ለሎሌው እንዳይሰጥህ ወደ እስር ቤት እንዳትገባ፤ ከባላጋራህ ጋር በመንገድ አብረኸው ስትሄድ ሳለህ ፈጥነህ ተስማማ፤