ኢዮብ 27:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በጽድቄ እጸናለሁ እርሱንም አልተውም፥ ከቀኖቼም ሁሉ ስለ አንዱም እንኳን ኅሊናዬ አይወቅሰኝም።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጽድቄን አጥብቄ እይዛለሁ፤ አልለቀውምም፤ በዘመኔም ሁሉ ኅሊናዬ አይወቅሠኝም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “በእውነተኛነቴ እጸናለሁ፤ እርሱንም አልተውም፤ በሕይወት በምኖርበት ዘመን ሁሉ ኅሊናዬ በዚህ ነገር አይወቅሰኝም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጽድቅን እየሠራሁ አልጠፋም፤ ያደረግሁት ክፉ ነገር አይታወቀኝምና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጽድቄን እይዛለሁ እርሱንም አልተውም፥ ከቀኖቼም ሁሉ ስለ አንዱ ልቤ አይዘልፈኝም። |
ጌታም ሰይጣንን፦ “በውኑ አገልጋዬን ኢዮብን ተመለከትኸውን? በምድር ላይ እንደ እርሱ ፍጹምና ቅን፥ እግዚአብሔርንም የሚፈራ፥ ከክፋትም የራቀ ሰው የለም፥ ያለ ምክንያት ይጠፋ ዘንድ በእርሱ ላይ ብትገፋፋኝም እንኳን፥ እስከ አሁን ፍጹምነቱን ጠብቋል።”
በመመካቴ ሞኝ ሆኜአለሁ! ይህ እናንተ ግድ ስላላችሁኝ የሆነ ነው። እኔ ከምንም የማልቆጠር ብሆን እንኳን፥ ከዋነኞቹ ሐዋርያት በምንም አላንስምና፥ በእርግጥም እናንተ ስለ እኔ መናገር ይገባችሁ ነበር።