Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢዮብ 17:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ጻድቅ ግን መንገዱን ያጠነክራል፥ እጁም ንጹሕ የሆነ ሰው ኃይልን እየጨመረ ይሄዳል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ጻድቃን ግን በያዙት መንገድ ይጸናሉ፤ ንጹሕ እጅ ያላቸውም እየበረቱ ይሄዳሉ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ይሁን እንጂ ጻድቃን ከእውነት መንገድ ፈቀቅ አይሉም፤ ንጹሖችም በብርታት ላይ ብርታትን ይጨምራሉ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ነገር ግን ወደ መን​ገዴ እንደ ምመ​ለስ እተ​ማ​መ​ና​ለሁ፤ እጆ​ችም የነጹ ናቸ​ውና፤ ደስ​ታ​ዬን አገ​ኛ​ታ​ለሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ጻድቅ ግን መንገዱን ያጠንክራል፥ እጁም ንጹሕ የሆነ ሰው ኃይልን እየጨመረ ይሄዳል።

Ver Capítulo Copiar




ኢዮብ 17:9
26 Referencias Cruzadas  

‘እኅቴ ናት’ ያለኝ እርሱ አይደለምን? እርሷም ደግሞ ራስዋ፥ ‘ወንድሜ ነው’ ብላኛለች፥ ይህንን በቅን ልብ እና በንጹሕ ኅሊና ነው ያደረግሁት”።


በዳዊት ቤትና በሳኦል ቤት መካከል የነበረው ጦርነት ለረጅም ጊዜ ቆየ፤ ሆኖም ዳዊት እያየለ ሲሄድ፥ የሳኦል ቤት ግን እየደከመ ነበር።


ንጹሑን ሰው ያድነዋል፥ በእጅህም ንጽሕና ትድናለህ።”


እናንተን ማጽደቅ ከእኔ ዘንድ ይራቅ፥ እስክሞት ድረስ ንጹሕነቴን ከእኔ አላርቅም።


በጽድቄ እጸናለሁ እርሱንም አልተውም፥ ከቀኖቼም ሁሉ ስለ አንዱም እንኳን ኅሊናዬ አይወቅሰኝም።”


እርምጃዬ ከመንገድ ወጥቶ፥ ልቤም ዓይኔን ተከትሎ፥ ነውርም ነገር ከእጄ ጋር ተጣብቆ እንደሆነ፥


‘እኔ ንጹሕ ነኝ፥ በደል የለብኝም፤ ያለ እንከን ነኝ፥ ኃጢአትም የለብኝም፥


መሠረቶቹ ከፈረሱ፥ ጻድቅ ምን ማድረግ ይችላል?


እጆቹ የነጹ፥ ልቡም ንጹሕ የሆነ፥ ነፍሱን ለከንቱ ያላነሣ፥ በሽንገላ ያልማለ።


እጆቼን በንጽሕና አጥባለሁ፥ አቤቱ፥ መሠዊያህን እዞራለሁ፥


እንዲህም አልሁ፦ በውኑ ልቤን በከንቱ አጸደቅሁ፥ እጆቼንም በንጽሕና በከንቱ አጠብሁ።


ከአእላፍ ይልቅ በአደባባዮችህ አንዲት ቀን ትሻላለች፥ በክፉዎች ድንኳኖች ከመቀመጥ ይልቅ፥ በእግዚአብሔር ቤት ደጃፍ ላይ መቅረትን መረጥሁ።


በልቅሶ ሸለቆ ውስጥ ሲያልፉ የምንጭ ቦታ ያደርጉታል፥ የበልግም ዝናብ በረከትን ይሰጣልና።


ከኃይል ወደ ኃይል ይሄዳሉ፥ የአማልክት አምላክ በጽዮን ይታያል።


ዐውሎ ነፋስ ሲያልፍ ክፉ ሰው አይገኝም፥ ጻድቅ ግን የዘለዓለም መሠረት ነው።


ጻድቅ ለዘለዓለም አይናወጥም፥ ክፉዎች ግን በምድር ላይ አይቀመጡም።


ጠቢብ ሰው ይፈራል ከክፉም ይሸሻል፥ ሰነፍ ግን ራሱን ታምኖ ይኰራል።


የጻድቃን መንገድ ግን እንደ ንጋት ብርሃን ነው፥ ሙሉ ቀን እስኪሆንም ድረስ እየተጨመረ ይበራል።


ከደቀ መዛሙርቱም አንዳንዶቹ ባልነጻ ማለትም ባልታጠበ እጅ እንጀራ ሲበሉ አዩ፤


ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ፤ እርሱም ወደ እናንተ ይቀርባል። እናንተ ኀጢአተኞች! እጃችሁን አንጹ፤ እናንተ በሁለት ሐሳብ የምትዋልሉ ልባችሁን አጥሩ።


ይህም ርስት በመጨረሻው ዘመን ይገለጥ ዘንድ ለተዘጋጀ መዳን በእምነት በእግዚአብሔር ኃይል ለተጠበቃችሁ ለእናንተ በሰማይ ተዘጋጅቶላችኋል።


ከእኛ ዘንድ ወጡ፥ ነገር ግን ከእኛ ወገን አልነበሩም፤ ከእኛ ወገንስ ቢሆኑ ኖሮ ከእኛ ጋር በኖሩ ነበር፤ ነገር ግን ሁሉ ከእኛ ወገን እንዳልሆኑ እንዲገለጥ ወጡ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos