2 ቆሮንቶስ 12:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)11 በመመካቴ ሞኝ ሆኜአለሁ! ይህ እናንተ ግድ ስላላችሁኝ የሆነ ነው። እኔ ከምንም የማልቆጠር ብሆን እንኳን፥ ከዋነኞቹ ሐዋርያት በምንም አላንስምና፥ በእርግጥም እናንተ ስለ እኔ መናገር ይገባችሁ ነበር። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም11 በመመካቴ ሞኝ ሆኛለሁ፤ ለዚህም ያበቃችሁኝ እናንተ ናችሁ፤ ስለ እኔ መመስከር የሚገባችሁ እናንተ ነበራችሁ። ደግሞም እኔ ከምንም የማልቈጠር ብሆንም፣ “ታላላቅ ሐዋርያት” ከሚባሉት በምንም አላንስም። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም11 እንደ ሞኝ ተናገርኩ! ታዲያ፥ እንዲህ እንድናገር ያደረጋችሁኝ እናንተ ናችሁ፤ እኔን ማመስገን የሚገባችሁ እናንተ ነበራችሁ፤ እኔ ማንነቴ ያልታወቀ ሰው ብሆንም እንኳ ታላላቅ ከተባሉት ሐዋርያት በምንም አላንስም። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)11 እነሆ እናንተ ስላገበራችሁኝ በመመካቴ ሰነፍ ሆንሁ፤ ለእኔማ በእናንተ ዘንድ ልከብርና እናንተም ምስክሮች ልትሆኑኝ ይገባኝ ነበር፤ እኔ እንደ ኢምንት ብሆንም ዋናዎቹ ሐዋርያት ሁሉ ከሠሩት ሥራ ያጐደልሁባችሁ የለምና። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)11 በመመካቴ ሞኝ ሆኜአለሁ፤ እናንተ ግድ አላችሁኝ፤ እናንተ እኔን ልታመሰግኑ ይገባ ነበርና። እኔ ምንም ባልሆን እንኳ፥ ከዋነኞቹ ሐዋርያት በምንም አልጎድልምና። Ver Capítulo |