ኢዮብ 27:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እናንተን ማጽደቅ ከእኔ ዘንድ ይራቅ፥ እስክሞት ድረስ ንጹሕነቴን ከእኔ አላርቅም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እናንተን እንደ ቅኖች መቍጠር፣ የማላደርገው ነገር ነው፤ ጨዋነቴንም እስክሞት ድረስ አልጥልም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናንተ የተናገራችሁት ሁሉ ትክክል ነው ብዬ በፍጹም አልቀበልም፤ እስከምሞትበት ቀን ድረስ በቅንነት መጽናቴን አልተውም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እናንተን ማጽደቅ ከእኔ ዘንድ ይራቅ፤ እስክሞትም ድረስ ፍጹምነቴን ከእኔ አላርቅምና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እናንተን ማጽደቅ ከእኔ ዘንድ ይራቅ፥ እስክሞት ድረስ ፍጹምነቴን ከእኔ አላርቅም። |
ጌታም ሰይጣንን፦ “በውኑ አገልጋዬን ኢዮብን ተመለከትኸውን? በምድር ላይ እንደ እርሱ ፍጹምና ቅን፥ እግዚአብሔርንም የሚፈራ፥ ከክፋትም የራቀ ሰው የለም፥ ያለ ምክንያት ይጠፋ ዘንድ በእርሱ ላይ ብትገፋፋኝም እንኳን፥ እስከ አሁን ፍጹምነቱን ጠብቋል።”
ጌታም ይህንን ለኢዮብ ከተናገረ በኋላ፥ ቴማናዊውን ኤልፋዝን እንዲህ አለው፦ “እንደ አገልጋዬ እንደ ኢዮብ ቅንን ነገር ስለ እኔ አልተናገራችሁምና ቁጣዬ በአንተና በሁለቱ ባልንጀሮችህ ላይ ነድዶአል።
ትምክህታችን ይህ ነው፦ በዚህ ዓለም ይልቁንም በእናንተ ዘንድ፥ በእግዚአብሔር ጸጋ እንጂ በሥጋዊ ጥበብ ባልሆነ፥ በእግዚአብሔር ቅድስናና ቅንነት እንደኖርን፥ የሕሊናችን ምስክርነት ነው።