Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢዮብ 27:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 እና​ን​ተን ማጽ​ደቅ ከእኔ ዘንድ ይራቅ፤ እስ​ክ​ሞ​ትም ድረስ ፍጹ​ም​ነ​ቴን ከእኔ አላ​ር​ቅ​ምና።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 እናንተን እንደ ቅኖች መቍጠር፣ የማላደርገው ነገር ነው፤ ጨዋነቴንም እስክሞት ድረስ አልጥልም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 እናንተን ማጽደቅ ከእኔ ዘንድ ይራቅ፥ እስክሞት ድረስ ንጹሕነቴን ከእኔ አላርቅም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 እናንተ የተናገራችሁት ሁሉ ትክክል ነው ብዬ በፍጹም አልቀበልም፤ እስከምሞትበት ቀን ድረስ በቅንነት መጽናቴን አልተውም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 እናንተን ማጽደቅ ከእኔ ዘንድ ይራቅ፥ እስክሞት ድረስ ፍጹምነቴን ከእኔ አላርቅም።

Ver Capítulo Copiar




ኢዮብ 27:5
17 Referencias Cruzadas  

እነሆ፥ ኀያሉ እጁን በእኔ ላይ ቢጭን፥ እርሱ እንደ ጀመረ እና​ገ​ራ​ለሁ፥ በፊ​ቱም እዋ​ቀ​ሳ​ለሁ።


ነገር ግን ወደ መን​ገዴ እንደ ምመ​ለስ እተ​ማ​መ​ና​ለሁ፤ እጆ​ችም የነጹ ናቸ​ውና፤ ደስ​ታ​ዬን አገ​ኛ​ታ​ለሁ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰይ​ጣ​ንን አለው፥ “በባ​ሪ​ያዬ በኢ​ዮብ ላይ እን​ዲህ እን​ዳ​ታ​ስብ ተጠ​ን​ቀቅ፤ በም​ድር ላይ እንደ እርሱ ያለ ገር፥ ጻድ​ቅና ንጹሕ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ፈራ፥ ከክ​ፋ​ትም ሁሉ የራቀ፥ ዳግ​መ​ኛም ቅን የሆነ ሰው የለ​ምና፤ አንተ ግን ሀብ​ቱን በከ​ንቱ አጠፋ ዘንድ ነገ​ር​ኸኝ።”


ብዙ ወራ​ትም ካለፈ በኋላ ሚስቱ እን​ዲህ አለ​ችው፥ “እስከ መቼ ትታ​ገ​ሣ​ለህ? 9 ‘ሀ’ ዳግ​መ​ኛም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጥቂት ወራት ደጅ እጠ​ና​ዋ​ለሁ፤ ዳግ​መ​ኛም መከ​ራ​ውን እታ​ገ​ሠ​ዋ​ለሁ፤ የቀ​ድ​ሞው ኑሬ​ዬ​ንም ተስፋ አደ​ር​ገ​ዋ​ለሁ ትላ​ለ​ህን? 9 ‘ለ’ እን​ደ​ዚ​ህስ እን​ዳ​ትል ከዚህ ዓለም እነሆ ስም አጠ​ራ​ርህ ጠፋ፤ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆቼም ሞቱ፥ ማኅ​ፀ​ኔም በምጥ ተጨ​ነቀ፥ በከ​ን​ቱም ደከ​ምሁ። 9 ‘ሐ’ አን​ተም በመ​ግ​ልና በትል ትኖ​ራ​ለህ፤ ሌሊ​ቱ​ንም ሁሉ ትዛ​ብ​ራ​ለህ። 9 ‘መ’ እኔ ግን እየ​ዞ​ርሁ እቀ​ላ​ው​ጣ​ለሁ። ከአ​ንዱ መን​ደር ወደ አንዱ መን​ደር፥ ከአ​ንዱ ቤትም ወደ አንዱ ቤት እሄ​ዳ​ለሁ፤ ከድ​ካ​ሜና በእኔ ላይ ካለ ችግ​ሬም ዐርፍ ዘንድ ፀሐይ እስ​ኪ​ገባ ድረስ እጠ​ብ​ቃ​ለሁ፤ ነገር ግን አሁን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስደ​ብና ሙት።”


ጽድ​ቅን ለበ​ስሁ፥ ቅን​ነ​ት​ንም እንደ መጎ​ና​ጸ​ፊያ ተሸ​ለ​ምሁ፤ ፍር​ድ​ንም እንደ ኩፋር ተቀ​ዳ​ጀ​ኋት


በእ​ው​ነ​ተኛ ሚዛን ልመ​ዘን፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቅን​ነ​ቴን ያው​ቃል።


እር​ም​ጃዬ ከመ​ን​ገዱ ፈቀቅ ብሎ እንደ ሆነ፥ ልቤም ዐይ​ኔን ተከ​ትሎ እንደ ሆነ፥ ጉቦም በእጄ ተጣ​ብቆ እንደ ሆነ፥


ኢዮ​ብም በፊ​ታ​ቸው ራሱን ጻድቅ አድ​ርጎ ነበ​ርና እነ​ዚያ ሦስቱ ወዳ​ጆቹ ለኢ​ዮብ ለመ​መ​ለስ ዝም አሉ።


ከአ​ው​ስ​ጢድ ሀገር ከአ​ራም ወገን የሆነ የቡ​ዛ​ዊው የባ​ር​ክ​ኤል ልጅ ኤሊ​ዩስ ተቈጣ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ራሱን ጻድቅ አድ​ርጎ ነበ​ርና ኢዮ​ብን ተቈ​ጣው።


ደግ​ሞም እንደ ኀጢ​አ​ተኛ አደ​ረ​ጉት እንጂ ለኢ​ዮብ የሚ​ገባ መልስ መመ​ለስ ስላ​ል​ቻሉ በሦ​ስቱ ባል​ን​ጀ​ሮቹ ላይ ተቈጣ።


እኔ ንጹሕ ነኝ፥ አል​በ​ደ​ል​ሁ​ምና፤ እኔ ጻድቅ ነኝ፥ ኀጢ​አ​ት​ንም አል​ሠ​ራ​ሁም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ይህን ቃል ለኢ​ዮብ ከተ​ና​ገረ በኋላ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቴማ​ና​ዊ​ውን ኤል​ፋ​ዝን እን​ዲህ አለው፥ “እንደ ባሪ​ያዬ እንደ ኢዮብ አን​ዲት ቅን ነገ​ርን በፊቴ አል​ተ​ና​ገ​ራ​ች​ሁ​ምና አን​ተና ሁለቱ ባል​ን​ጀ​ሮ​ችህ በድ​ላ​ች​ኋል።


አሁ​ንም ተቀ​መጡ፤ በደ​ልም አይ​ኑር፤ ዳግ​መ​ኛም ከጻ​ድቁ ጋር አንድ ሁኑ።


ኃጥኡን ጻድቅ፥ ጻድቁንም ኃጥእ ብሎ መፍረድ በእግዚአብሔር ዘንድ የረከሰና የተናቀ ነው።


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቸር​ነ​ትና ይቅ​ርታ መመ​ኪ​ያ​ች​ንና የነ​ፃ​ነ​ታ​ችን ምስ​ክር ይህቺ ናትና፥ በሥ​ጋዊ ጥበብ ሳይ​ሆን፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸጋ በዚህ ዓለም፥ ይል​ቁ​ንም በእ​ና​ንተ ዘንድ ተመ​ላ​ለ​ስን።


ነገር ግን ኬፋ ወደ አን​ጾ​ኪያ በመጣ ጊዜ ፊት ለፊት ተቃ​ወ​ም​ሁት፤ ነቅ​ፈ​ውት ነበ​ርና።


“በሰ​ዎች መካ​ከል ጠብ ቢሆን፥ ወደ ፍር​ድም ቢመጡ፥ ቢፋ​ረ​ዱም ለጻ​ድቁ ይፈ​ረ​ድ​ለት፤ በበ​ደ​ለ​ኛ​ውም ይፈ​ረ​ድ​በት።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos