ኢዮብ 23:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ዛሬም ደግሞ የኀዘን እንጉርጉሮዬ ገና መራራ ነው፥ በመቃተት ብጮኽም እጁ በእኔ ላይ እንደ ከበደች ናት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ዛሬም ሐዘኔ መራራ ነው፤ እያቃሰትሁ እንኳ እጁ በላዬ ከብዳለች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “አሁንም ልቤ በመረረ ሐዘንና ሮሮ የተሞላ ነው፤ በመቃተት ብጮኽም እጁ በእኔ ላይ እንደ ከበደች ናት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ዛሬም ዘለፋዬ ከእጄ እንደ ሆነ ዐወቅሁ። እጁንም በእኔ ላይ አከበደ፥ አስለቀሰኝም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዛሬም ደግሞ የኅዘን እንጕርጕሮዬ ገና መራራ ነው፥ እጁ በልቅሶ ጩኸቴ ላይ ከብዳለች። |