Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሕዝቅኤል 24:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 የሰው ልጅ ሆይ፥ እነሆ የዐይንህን ምኞት በቅፅበት እወስድብሃለሁ፤ ቢሆንም ግን ዋይታ አታሰማ፥ አታልቅስ፥ እንባህንም አታፍስስ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 “የሰው ልጅ ሆይ፤ የዐይንህ ማረፊያ የሆነውን ነገር በመቅሠፍት እወስድብሃለሁ፤ አንተ ግን ዋይታ አታሰማ፤ አታልቅስ፤ እንባህንም አታፍስስ፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 “የሰው ልጅ ሆይ! የምትወዳትና የዐይንህ መደሰቻ የሆነችው ሚስትህ ተቀሥፋ በድንገት ትሞትብሃለች፤ በዚህም አትዘን፤ እንባህንም በማፍሰስ አታልቅስ፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 “የሰው ልጅ ሆይ! እነሆ የዐ​ይ​ን​ህን አም​ሮት በመ​ቅ​ሠ​ፍት እወ​ስ​ድ​ብ​ሃ​ለሁ፤ አን​ተም ዋይ አት​በል፤ አታ​ል​ቅ​ስም፤ እን​ባ​ህ​ንም አታ​ፍ​ስስ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 የሰው ልጅ ሆይ፥ እነሆ፥ የዓይንህን አምሮት በመቅሠፍት እወስድብሃለሁ፥ አንተም ወይ አትበል አታልቅስም እንባህንም አታፍስስ።

Ver Capítulo Copiar




ሕዝቅኤል 24:16
17 Referencias Cruzadas  

“ዛሬም ደግሞ የኀዘን እንጉርጉሮዬ ገና መራራ ነው፥ በመቃተት ብጮኽም እጁ በእኔ ላይ እንደ ከበደች ናት።


ሀብት ወደ ስድብ አስቶ እንዳይወስድህ፥ ትልቅ ጉቦም ከመስመር እንዳያስወጣህ።


እንደ ተወደደች ዋላ እንደ ተዋበችም ሚዳቋ፥ ጡትዋ ሁልጊዜ ታርካህ፥ በፍቅርዋም ሁልጊዜ ጥገብ።


እኔ የውዴ ነኝ፥ የእርሱም ምኞት ወደ እኔ ነው።


ይህን ባትሰሙ ነፍሴ ስለ ትዕቢታችሁ በስውር ታለቅሳለች፤ የጌታም መንጋ ተማርኮአልና ዓይኔ እጅግ ታነባለች፥ እንባንም ታፈስሳለች።


“ጌታ እንዲህ ይላል፦ ሰላሜን፥ ቸርነትንና ጽኑ ፍቅርን፥ ከዚህ ሕዝብ አስወግጄአለሁና ልቅሶ ወዳለበት ቤት አትግባ፥ ለማልቀስም ሆነ ለማዘን አትሂድ።


የተወለደባትንም አገር ለማየት ከእንግዲህ ወዲህ አይመለስምና ለሚሄደው እጅግ አልቅሱ እንጂ ለሞተው አታልቅሱ አትዘኑለትም።


ስለዚህ ጌታ ስለ ይሁዳ ንጉሥ ስለ ኢዮስያስ ልጅ ስለ ኢዮአቄም እንዲህ ይላል፦ “ ‘ወንድሜ ሆይ! ወዮ! እህቴ ሆይ! ወዮ!’ እያሉ አያለቅሱለትም፥ ወይም፦ ‘ጌታ ሆይ! ወዮ! ግርማዊነቱ ሆይ! ወዮ!’ እያሉ አያለቅሱለትም።


ተወግተው ስለ ሞቱት ስለ ሕዝቤ ሴት ልጅ ሰዎች ሌሊትና ቀን እንዳለቅስ ራሴ ውኃ፥ ዓይኔም የእንባ ምንጭ በሆነልኝ!


ዐይኖቻችንም እንባ እንዲያፈስሱ የዓይናችንም ሽፋሽፍቶች ውኃን እንዲያፈልቁ ፈጥነው ለእኛ ልቅሶውን ያነሳሱ።


ጻዴ። ልባቸው ወደ ጌታ ጮኸ፥ የጽዮን ሴት ልጅ ቅጥር ሆይ፥ እንባሽን እንደ ፈሳሽ ቀንና ሌሊት አፍስሺ፥ ለሰውነትሽ ዕረፍት አትስጪ፥ የዐይንሽ ብሌን አታቋርጥ።


የጌታ ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፦


እኔም በማለዳ ለሕዝቡ ተናገርሁ፥ ማታም ሚስቴ ሞተች፤ በማግስቱም እንደ ታዘዝሁ አደረግሁ።


በሕዝቡ መካከል ያሚገኝ አለቃ የረከሰ እዳይሆን ራሱን አያርክስ።


ነገር ግን ወንድሞች ሆይ! አንቀላፍተው ስላሉት፥ ተስፋ እንደሌላቸው እንደ ሌሎች ሰዎች ደግሞ ልታዝኑ እንደማይገባ ልናሳውቃችሁ እንወዳለን።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos