ኢዮብ 23:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱ ግን የሚተካከለው የለውም፥ ማንስ ውሳኔውን ያስቀይረዋል? የወደደውንም ያደርጋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እርሱ ግን ራሱን ችሎ ብቻውን የሚኖር ነው፤ የሚቋቋመውስ ማን ነው? እርሱ የፈቀደውን ያደርጋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እርሱ ራሱ ይወስናል፤ እርሱንም የሚቃወም የለም፤ እርሱ የወደደውን ሁሉ ያደርጋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ስለ ፍርድ የሚከራከር ማን ነው? እርሱ የወደደውን ያደርጋልና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱ ግን ብቻውን ነው፥ እርሱንስ የሚመስለው ማን ነው? ነፍሱም የወደደችውን ያደርጋል። |
እግዚአብሔር የሚያደርገው ሁሉ ለዘለዓለም እንደሚኖር አወቅሁ፥ ምንም የሚጨመርበት ወይም የሚቀነስለት የለም፥ እግዚአብሔርም ሰዎች ይፈሩ ዘንድ አደረገ።