Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢዮብ 34:29 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

29 ሕዝብንም ሆነ ሰውን በተመለከተ፥ ዝም ቢል የሚፈርድ ማን ነው? ፊቱንስ ቢሰውር የሚያየው ማን ነው?

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

29 እርሱ ዝም ቢል፣ ማን ሊፈርድ ይችላል? ፊቱንስ ቢሰውር፣ ማን ሊያየው ይችላል? እርሱ ከሰውም፣ ከሕዝብም በላይ ነው፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

29-30 “እግዚአብሔርን የሚክድና ሕዝቡን የሚያጠምድ ንጉሥ ሲነግሥ፥ እግዚአብሔር ዝም ቢል፥ ወይም ፊቱን ቢሰውር ማን ሊወቅሰው ይችላል?

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

29 “እርሱ ዕረ​ፍ​ትን ይሰ​ጣል፤ የሚ​ፈ​ር​ድስ ማን ነው? በሕ​ዝብ ወይም በሰው ዘንድ ፊቱን ቢሰ​ውር የሚ​ያ​የው ማን ነው?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

29 በሕዝብ ወይም በሰው ዘንድ ቢሆን፥ እርሱ ቢያሳርፍ የሚፈርድ ማን ነው? ፊቱንስ ቢሰውር የሚያየው ማን ነው?

Ver Capítulo Copiar




ኢዮብ 34:29
26 Referencias Cruzadas  

በአንተ ለምትደገፍ ነፍስ በአንተ ላይ ታምናለችና በሰላም ትጠብቃታለህ።


እርሱ ግን የሚተካከለው የለውም፥ ማንስ ውሳኔውን ያስቀይረዋል? የወደደውንም ያደርጋል።


ሰላምን እተውላችኋለሁ፤ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ፤ እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጠው ዓይነት አይደለም። ልባችሁ አይታወክ፤ አይፍራም።


የጽድቅም ሥራ ሰላም፥ የጽድቅም ፍሬ ለዘለዓለም ጸጥታና መታመን ይሆናል።


ፊትህን ከእኔ አትሰውር፥ ተቈጥተህ ከባርያህ ፈቀቅ አትበል፥ ረዳት ሁነኝ፥ አትጣለኝም፥ የመድኃኒቴም አምላክ ሆይ፥ አትተወኝ።


ከሰውም ማስተዋል ሁሉ በላይ የሆነው የእግዚአብሔር ሰላም ልባችሁንና አሳባችሁን በክርስቶስ ኢየሱስ ይጠብቃል።


ነገር ግን ለባቢሎን ንጉሥም ለናቡከደነፆር የማያገለግለውን፥ ከባቢሎንም ንጉሥ ቀንበር በታች አንገቱን ዝቅ የማያደርገውን ሕዝብና መንግሥት፥ በእጁ እስካጠፋው ድረስ በሰይፍና በራብ በቸነፈርም ያን ሕዝብ እቀጣለሁ፥ ይላል ጌታ።


አቤቱ፥ ፈጥነህ ስማኝ፥ መንፈሴ ዛለ፥ ፊትህን ከኔ አትሰውር፥ ወደ ጉድጓድም እንደሚወርዱ እንዳልሆን።


እኔም በደስታዬ፦ ለዘለዓለም አልታወክም አልሁ።


ለመዘምራን አለቃ፥ የዳዊት መዝሙር።


እነሆ፥ ካፈረሰ፥ የፈረሰው ተመልሶ አይሠራም፥ በሰውም ላይ ከዘጋ፥ ሊከፈት አይችልም።


ንጉሡ በቤተ መንግሥቱ ከተቀመጠና ጌታም በዙሪያው ካሉት ጠላቶቹ ሁሉ ካሳረፈው በኋላ፥


ይህም እግዚአብሔርን የሚክድ እንዳይነግሥ፥ በሕዝቡም ላይ ወጥመድ የሚዘረጋ እንዳይኖር ነው።


እርሱም “እኔ ከአንተ ጋር እሄዳለሁ፥ ዕረፍትም እሰጥሃለሁ” አለው።


ለሕዝቤ ለእስራኤል መሪዎች ከሾምሁለት ጊዜ አንሥቶ እንዳደረጉበት ከእንግዲህ አያደርጉበትም፤ ከጠላቶችህ ሁሉ አሳርፍሃለሁ። ከዚህም በላይ ጌታ ራሱ ቤት እንደሚሠራልህ ይነግርሃል፤


የኢዮሣፍጥም መንግሥት ጸጠጥታ ሰፈነበት፥ አምላኩም በዙርያው ካሉ አሳረፈው።


አሕዛብንስ የሚገሥጸው፥ ለሰውም እውቀት የሚያስተምረው እርሱ አይቀጣምን?


እኔ ራሴ በጎቼን አሰማራለሁ አስመስጋቸዋለሁም፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios