Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -


መዝሙር 115 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ለእኛ አይደለም፥ አቤቱ፥ ለእኛ አይደለም፥ ነገር ግን ለስምህ ስለ ጽኑ ፍቅርህና ስለ እውነትህም ክብርን ስጥ።

2 አሕዛብ፦ “አምላካቸው ወዴት ነው?” ለምን ይበሉ?

3 አምላካችንስ በላይ በሰማይ ነው፥ የፈቀደውን ሁሉ አደረገ።

4 የአሕዛብ ጣዖታቶች የወርቅና የብር፥ የሰው እጅ ሥራ ናቸው።

5 አፍ አላቸው አይናገሩምም፥ ዐይን አላቸው አያዩምም፥

6 ጆሮ አላቸው አይሰሙምም፥ አፍንጫ አላቸው አያሸትቱምም፥

7 እጅ አላቸው አይዳስሱምም፥ እግር አላቸው አይሄዱምም፥ በጉሮሮአቸውም ድምፅ አያሰሙም።

8 የሚሠሩአቸው፥ የሚያምኑባቸውም ሁሉ እንደ እነርሱ ይሁኑ።

9 የእስራኤል ቤት ሆይ፥ በጌታ ታመኑ፥ ረድኤታቸውና መከታቸው እርሱ ነው።

10 የአሮን ቤት ሆይ፥ በጌታ ታመኑ፥ ረድኤታቸውና መከታቸው እርሱ ነው።

11 ጌታን የምትፈሩ፥ በጌታ ታመኑ፥ ረድኤታቸውና መከታቸው እርሱ ነው።

12 ጌታ አሰበን፥ ይባርከንማል፥ የእስራኤልን ቤት ይባርካል፥ የአሮንንም ቤት ይባርካል።

13 ጌታን የሚፈሩትን፥ ትንንሾችንና ትልልቆችን ይባርካል።

14 ጌታ በላያችሁ፥ በላያችሁና በልጆቻችሁ ላይ ይጨምር።

15 እናንተ ሰማይንና ምድርን በሠራ ጌታ የተባረካችሁ ሁኑ።

16 ሰማያት የጌታ ሰማያት ናቸው፥ ምድርን ግን ለሰው ልጆች ሰጣት።

17 አቤቱ፥ ሙታን የሚያመሰግኑህ አይደሉም፥ ወደ ሲኦልም የሚወርዱ ሁሉ፥

18 እኛ ሕያዋን ግን ከአሁን ጊዜ ጀምሮ እስከ ዘለዓለም ጌታን እንባርካለን። ሃሌ ሉያ።

Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos