ኢዮብ 21:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ስሙ፥ ቃሌን ስሙ፥ ይህም እንደ ማጽናናት ይቆጠርላችሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ቃሌን በጥንቃቄ ስሙ፤ የምታጽናኑኝም በዚህ ይሁን፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እስቲ ንግግሬን በጥሞና አድምጡኝ፤ በዚህም እኔን እንዳጽናናችሁኝ ይቈጠርላችሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “እኛ አጽናናነው እንዳትሉኝ፥ ስሙ፤ ቃሌን ስሙ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስሙ፥ ቃሌን ስሙ፥ ይህም መጽናናታችሁ ይሁን። |
እንጀራ ላልሆነ ነገር ገንዘብን ለምን ታባክናላችሁ፥ የድካማችሁንም ዋጋ በማያጠግብ ነገር ለምን ትለውጣላችሁ? አድምጡኝ፥ በረከትንም ብሉ፥ ሰውነታችሁም በጮማ ደስ ይበለው።
ኢዮአታም ይህ በተነገረው ጊዜ፥ በገሪዛን ተራራ ጫፍ ላይ ወጥቶ ድምጽን ከፍ በማድረግ እንዲህ አላቸው፤ የሴኬም ነዋሪዎች ሆይ፥ እግዚአብሔር ይሰማችሁ ዘንድ እኔን ስሙኝ፤