ኢዮብ 19:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነሆ፥ ስለ ተደረገብኝ ግፍ ብጮኽ ማንም አይመልስልኝም፥ ድረሱልኝ ብዬ ብጣራ ፍርድ የለኝም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘ተበደልሁ’ ብዬ ብጮኽ ማንም አይመልስልኝም፤ ድምፄን ከፍ አድርጌ ባሰማም፣ ፍትሕ አላገኝም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ተበደልኩ ብዬ ብጮኽ የሚሰማኝ አላገኘሁም፤ ድምፄን ከፍ አድርጌ አቤቱታ ባሰማም ፍትሕ አላገኘሁም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነሆ፥ በዘለፋ እደክማለሁ፤ አልናገርምም፤ አሰምቼም እጮኻለሁ፤ ነገር ግን ፍርድ የለኝም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነሆ፥ ስለ ተደረገብኝ ግፍ ብጮኽ ማንም አይመልስልኝም፥ አሰምቼም ብጠራ ፍርድ የለኝም። |