Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢዮብ 9:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 ምድር በኃጥአን እጅ ተሰጥታለች፥ የፈራጆችዋን ፊት ሸፍኖአል፥ ይህንን ያደረገው እርሱ ካልሆነ ሌላ ማን ነው?”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 ምድር በክፉዎች እጅ ስትወድቅ፣ እርሱ የፈራጆቿን ዐይን ይሸፍናል፤ ታዲያ፣ ይህን ያደረገው እርሱ ካልሆነ ማን ሊሆን ይችላል?

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 ምድር በክፉ ሰዎች እጅ ተላልፋ ስትሰጥ እርሱ የዳኞችን ዐይን ይሸፍናል፤ ይህን ያደረገ እግዚአብሔር ካልሆነ ታዲያ፥ ማነው?

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 በኃ​ጥ​ኣን እጅ ተሰ​ጥ​ተ​ዋ​ልና፤ የም​ድር ፈራ​ጆ​ችን ፊት ይሸ​ፍ​ናል፤ እርሱ ካል​ሆነ ማን ነው?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 ምድር በኃጥአን እጅ ተሰጥታለች፥ የፈራጆችዋን ፊት ሸፍኖአል፥ እርሱ ካልሆነ ማን ነው?

Ver Capítulo Copiar




ኢዮብ 9:24
24 Referencias Cruzadas  

ዳዊት ግን እያለቀሰ፥ ራሱን ተከናንቦ፥ ባዶ እግሩን የደብረ ዘይትን ተራራ ወጣ፤ አብሮት ያለውም ሕዝብ ሁሉ እንደዚሁ ራሱን ተከናንቦ እያለቀሰ ተራራውን ይወጣ ነበር።


በዚያችም ዕለት ከጦርነት ሸሽቶ በኀፍረት እየተሸማቀቀ ወደ ከተማ እንደሚገባ ሰው ሕዝቡም ድምፅ ሳያሰማ ወደ ከተማ ገባ።


ልታስጨንቅና የእጅህን ሥራ ልትንቅ የክፉዎችንስ ምክር ልታበራ በአንተ ዘንድ መልካም ነውን?


አማካሪዎችንም እራቁታቸውን ይሰዳቸዋል፥ ፈራጆችንም ሞኝ ያደርጋል።


እግዚአብሔር ለጠማማ ሰው አሳልፎ ሰጠኝ፥ በክፋዎችም እጅ ጣለኝ።


እነሆ፥ ስለ ተደረገብኝ ግፍ ብጮኽ ማንም አይመልስልኝም፥ ድረሱልኝ ብዬ ብጣራ ፍርድ የለኝም።


ኃይለኛ ሰው መሬት ገዛ፥ የተከበረ ሰው ተቀመጠባት።


በከተማው ለመሞት የሚያጣጥሩ ያቃስታሉ፥ ቁስለኞችም ለእርዳታ ይጮኻሉ፥ እግዚአብሔር ግን ልመናቸውን አይመለከትም።”


እንዲህስ ባይሆን ሐሰተኛ የሚያደርገኝ፥ ነገሬንስ እንደ ከንቱ የሚያደርገው ማን ነው?”


ከራም ወገን የሆነ የቡዛዊው የባርክኤል ልጅ የኤሊሁ ቁጣ ነደደ፥ ከእግዚአብሔር ይልቅ ራሱን ጻድቅ አድርጎ ነበርና ኢዮብን ተቈጣው።


አቤቱ፥ ከሰዎች፥ እድል ፈንታቸው በሕይወታቸው ከሆነች ከዚህ ዓለም ሰዎች በእጅህ አድነኝ፥ ከሰወርኸው መዝገብህ ሆዳቸውን አጠገብህ፥ ልጆቻቸው ተትረፍርፎላቸዋል የተረፋቸውንም ለሕፃናቶቻቸው ያተርፋሉ።


እኔም ተመለስሁ፥ ከፀሐይ በታችም የሚደረገውን ግፍ ሁሉ አየሁ፥ እነሆም፥ የተገፉት ሰዎች እንባ፥ የሚያጽናናቸውም አልነበረም፥ በሚገፉአቸውም እጅ ኃይል ነበረ፥ እነርሱን ግን የሚያጽናናቸው አልነበረም።


በምድር ላይ አልዘነበምና መሬቱ ስንጥቅጥቅ ስለሆነ አራሾች አፈሩ ራሳቸውንም ተከናነቡ።


በቃላችሁ ጌታን አሰልችታችሁታል። እናንተም፦ እርሱን ያሰለቸነው በምንድን ነው? ትላላችሁ። “ክፉን የሚያደርግ ሁሉ በጌታ ፊት መልካም ነው፥ እርሱም በእነርሱ ደስ ይለዋል” ወይም “የፍትሕ አምላክ የት አለ?” በማለታችሁ ነው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos