ኢዮብ 12:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለባልንጀራው መሳለቂያ እንደሚሆን ሰው ሆኛለሁ፥ እግዚአብሔርን የጠራሁ እኔ፥ እርሱም የመለሰልኝ፥ ጻድቅና ፍጹም ሰው መሳለቂያ ሆኖአል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እግዚአብሔርን ጠርቼ የመለሰልኝ ሰው ብሆንም፣ ለባልንጀሮቼ መሣቂያ ሆኛለሁ፤ ጻድቅና ያለ ነቀፋ ሆኜ እያለሁ፣ መሣቂያ ሆኛለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔርን ጠርቼው የመለሰልኝ ጊዜ ነበር፤ አሁን እኔ የወዳጆቼ መሳቂያ ሆኛለሁ፤ ስሕተት የሌለብኝ ፍጹሙ እኔ የሰው ሁሉ መሳለቂያ ሆኛለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርን የጠራሁ እርሱም የመለሰልኝ እኔ፥ ለባልንጀራው መሣለቂያ እንደሚሆን ሰው ሆኛለሁ፤ ጻድቁና ንጹሑ ሰው መሣለቂያ ሆኖአል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርን የጠራሁ እርሱም የመለሰልኝ እኔ ለባልንጀራው መሳለቂያ እንደሚሆን ሰው ሆኛለሁ፥ ጻድቅና ፍጹም ሰው መሳለቂያ ሆኖአል። |
ኢዮብም፦ በእግዚአብሔር መደሰት ለሰው ምንም አይጠቅምም ብሏልና፥ ከበደለኞች ጋር የሚተባበር፥ ክፉ ከሚያደርጉስ ጋር የሚሄድ፥ ሹፈትን እንደ ውኃ የሚጠጣት እንደ ኢዮብ ያለ ሰው ማን ነው?”
የእሾህ አክሊል ጐንጉነው በራሱ ላይ፥ በቀኝ እጁም መቃ አኖሩ፤ በፊቱም ተንበርክከው “የአይሁድ ንጉሥ ሆይ! ሰላም ለአንተ ይሁን” እያሉ አፌዙበት፤