Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢዮብ 11:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ከንቱ ልፍለፋህ ሰዎችን ዝም ያሰኛቸዋልን? ብትሳለቅስ የሚያሳፍርህ የለምን?

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 በውኑ የአንተ መዘላበድ ሰውን ዝም ያሰኛልን? ስታፌዝስ የሚገሥጽህ የለም?

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ኢዮብ ሆይ! ከንቱ ንግግርህ መልስ የማይሰጥበት ይመስልሃልን? ይህን ያኽልስ ስታፌዝ፥ የሚገሥጽህ የሌለ መሰለህን?

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ንግ​ግር አታ​ብዛ፤ የሚ​ከ​ራ​ከ​ርህ የለ​ምና።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ትምክህትህስ ሰዎችን ዝም ያሰኛቸዋልን? ብትሳለቅስ የሚያሳፍርህ የለምን?

Ver Capítulo Copiar




ኢዮብ 11:3
14 Referencias Cruzadas  

አላጋጮች በእኔ ዘንድ አሉ፥ ዓይኔም ማስቈጣታቸውን ትመለከታለች።


እነርሱ “በመጨረሻው ዘመን ክፉ ምኞታቸውን የሚከተሉ ተሳላቂዎች ይሆናሉ፤” ብለዋችኋልና።


የሚቃወም ሰው ስለ እኛ የሚናገረውን መጥፎ ነገር ሲያጣ እንዲያፍር እውነተኛና የማይነቀፍ ቃልን ተናገር።


በዚህ መልእክት በኩል ለተላከው ቃላችን የማይታዘዝ ማንም ቢኖር፥ ይህን ሰው በምልክት ለዩት፤ እንዲያፍርም ከእርሱ ጋር አትተባበሩ።


በዋዘኞች ጉባኤ አልተቀመጥኩም አልተደሰትኩምም፤ ቁጣን ሞልተህብኛልና እጅህ በእኔ ላይ ስለ ሆነ ለብቻዬ ተቀመጥሁ።


እንዲሁ በቁጣህ አሳድዳቸው፥ በመቅሠፍትህም አስደንግጣቸው።


ፈተኑኝ በሣቅም ዘበቱብኝ፥ ጥርሳቸውንም በእኔ ላይ አንቀጫቀጩ።


ኢዮብም፦ በእግዚአብሔር መደሰት ለሰው ምንም አይጠቅምም ብሏልና፥ ከበደለኞች ጋር የሚተባበር፥ ክፉ ከሚያደርጉስ ጋር የሚሄድ፥ ሹፈትን እንደ ውኃ የሚጠጣት እንደ ኢዮብ ያለ ሰው ማን ነው?”


እንዲህስ ባይሆን ሐሰተኛ የሚያደርገኝ፥ ነገሬንስ እንደ ከንቱ የሚያደርገው ማን ነው?”


እናገር ዘንድ ተውኝ፥ ከተናገርሁም በኋላ ተሳለቁ።


ቢመረምራችሁስ መልካም ይሆንልችኋልን? ወይስ በሰውን እንደምታታልሉ ልታታልሉት ትፈልጋላችሁን?


እናንተ ግን በሐሰት ለባጮች ናችሁ፥ ሁላችሁም የማትጠቅሙ ሐኪሞች ናችሁ።


ለባልንጀራው መሳለቂያ እንደሚሆን ሰው ሆኛለሁ፥ እግዚአብሔርን የጠራሁ እኔ፥ እርሱም የመለሰልኝ፥ ጻድቅና ፍጹም ሰው መሳለቂያ ሆኖአል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios