ኤርምያስ 7:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መንገዳችሁንና ሥራችሁን ፈጽማችሁ ብታሳምሩ፥ በሰውና በጎረቤቱ መካከል ቅን ፍርድ ብትፈርዱ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም መንገዳችሁንና ሥራችሁን በርግጥ ብታሳምሩ፣ በመካከላችሁ ቅንነት ቢኖር፣ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ይልቅስ የአኗኗራችሁንና የተግባራችሁን ሁኔታ ለውጡ፤ እርስ በርሳችሁ ቅንነት በሞላበት ፍቅር ተሳስራችሁ ኑሩ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መንገዳችሁንና ሥራችሁን ፈጽማችሁ ብታቃኑ፥ በሰውና በጓደኛው መካከል ቅን ፍርድ ብትፈርዱ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መንገዳችሁንና ሥራችሁን ፈጽማችሁ ብታሳምሩ፥ በሰውና በጎረቤቱ መካከል ቅን ፍርድ ብትፈርዱ፥ |
የዳዊት ቤት ሆይ! ጌታ እንዲህ ይላል፦ ‘ስለ ሥራችሁ ክፋት ቁጣዬ እንደ እሳት እንዳይወጣና ማንም ሳያጠፋው እንዳይነድድ፥ በማለዳ ፍርድን አድርጉ፥ የተበዘበዘውንም ከጨቋኙ እጅ አድኑ።’
በዝግባ እንጨት ስለምትወዳደር በውኑ ትነግሣለህን? በውኑ አባትህ ይበላና ይጠጣ ፍርድንና ጽድቅን ያደርግ አልነበረምን? በዚያም ጊዜ መልካም ሆኖለት ነበር።
ጌታ እንዲህ ይላል፦ ፍርድንና ጽድቅን አድርጉ የተበዘበዘውንም ከአስጨናቂው እጅ አድኑ፤ መጻተኛውንና ድሀ አደጉን መበለቲቱንም አትበድሉ፥ አታምፁባቸውም፥ በዚህም ስፍራ ንጹሕ ደምን አታፍስሱ።
ድሀ ከመበደል እጁን ቢመልስ፥ አራጣ ወይም ትርፍ ባይወስድ፥ ፍርዴን ቢያደርግ፥ በትእዛዜም ቢሄድ፥ እርሱ በእርግጥ በሕይወት ይኖራል እንጂ በአባቱ ኃጢአት አይሞትም።
ኢየሩሳሌምና በዙሪያዋ ያሉ ከተሞች ገና ሰዎች እየኖሩባቸው፥ በሰላም ተቀምጠው እያሉ፥ ደቡቡና ቈላውም ሰዎች እየኖሩባቸው በነበረ ጊዜ አይደለም እንዴ፥ ይህንን ቃል ጌታ በቀደሙት ነቢያት አማካኝነት የተናገረው?
በያቤሽ ገለዓድ ከሚኖረው ሕዝብ መካከል ወንድ ያልደረሰባቸው አራት መቶ ደናግል አገኙ፤ በከነዓን ምድር በሴሎ ወደሚገኘውም ሰፈር አመጧቸው።