ሕዝቅኤል 18:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)17 ድሀ ከመበደል እጁን ቢመልስ፥ አራጣ ወይም ትርፍ ባይወስድ፥ ፍርዴን ቢያደርግ፥ በትእዛዜም ቢሄድ፥ እርሱ በእርግጥ በሕይወት ይኖራል እንጂ በአባቱ ኃጢአት አይሞትም። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም17 እጁን ደኻን ከመበደል ቢሰበስብ፣ ዐራጣ ወይም ከፍተኛ ወለድ ባይቀበል፣ ሕጌን ቢጠብቅ፣ ሥርዐቴንም ቢከተል፣ በሕይወት ይኖራል እንጂ በአባቱ ኀጢአት አይሞትም። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም17 በድኾች ላይ ምንም ዐይነት ግፍ ባይሠራ፥ ገንዘቡን በአራጣ አበድሮ ከፍተኛ ወለድ ባያስከፍል፥ ሕጌን ቢያከብር፥ ሥርዓቴን ቢከተል፥ እንዲህ ዐይነቱ ሰው በእርግጥ በሕይወት ይኖራል እንጂ አባቱ በሠራው ኃጢአት ምክንያት አይሞትም። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)17 እጁንም ከዐመፅ ቢመልስ፥ አራጣንም አትርፎ ባይወስድ፥ ፍርዴንም ቢያደርግ፥ በትእዛዜም ቢሄድ፥ እርሱ ፈጽሞ በሕይወት ይኖራል እንጂ በአባቱ ኀጢአት አይሞትም። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)17 እጁንም ድሀን ከመበደል ቢመልስ አራጣን ትርፎቻንም ባይወስድ ፍርዴንም ቢያደርግ በትእዛዜም ቢሄድ፥ እርሱ ፈጽሞ በሕይወት ይኖራል እንጂ በአባቱ ኃጢአት አይሞትም። Ver Capítulo |