በኢየሩሳሌምም ነቢያት መካከል አስደንጋጭ ነገር አይቻለሁ፤ ያመነዝራሉ በሐሰትም ይሄዳሉ፤ ማንም ከክፋቱ እንዳይመለስ የክፉ አድራጊዎችን እጅ ያበረታሉ፤ ሁላቸውም እንደ ሰዶም የሚኖሩባትም እንደ ገሞራ ሆኑብኝ።
ኤርምያስ 23:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በምክሬ ግን ቢቆሙ ኖሮ፥ ለሕዝቤ ቃሎቼን ባሰሙ ነበር፥ ከክፉም መንገዳቸው ከሥራቸውም ክፋት በመለሱአቸው ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምክሬ ባለበት ቢቆሙ ኖሮ፣ ቃሌን ለሕዝቤ ባሰሙ ነበር፤ ከክፉ መንገዳቸው፣ ከክፉ ሥራቸውም በመለሷቸው ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእኔ ጉባኤ ፊት ቆመው ቢሆንማ ኖሮ ቃሌን ለሕዝቡ ባወጁ ነበር፤ ጠማማ መንገዳቸውንና ክፉ አኗኗራቸውንም ትተው ወደ እኔ እንዲመለሱ ማድረግ በቻሉ ነበር።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በቃሌ ቢቆሙና ምክሬን ቢሰሙ ኖሮ ግን ሕዝቤን ከክፉ ሥራቸው በመለሱአቸው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በምክሬ ግን ቢቆሙ ኖሮ፥ ለሕዝቤ ቃሌን ባሰሙ ነበር፥ ከክፉም መንገዳቸው ከሥራቸውም ክፋት በመለሱአቸው ነበር። |
በኢየሩሳሌምም ነቢያት መካከል አስደንጋጭ ነገር አይቻለሁ፤ ያመነዝራሉ በሐሰትም ይሄዳሉ፤ ማንም ከክፋቱ እንዳይመለስ የክፉ አድራጊዎችን እጅ ያበረታሉ፤ ሁላቸውም እንደ ሰዶም የሚኖሩባትም እንደ ገሞራ ሆኑብኝ።
እርሱም፦ ሁላችሁ እናንተ ከክፉ መንገዳችሁና ከሥራችሁ ክፋት ተመለሱ፤ ጌታም ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ለእናንተና ለአባቶቻችሁ በሰጣችሁ ምድር ተቀመጡ።
እንዲሁም፦ ‘እያንዳንዳችሁ ከክፉ መንገዳችሁ ተመለሱ፥ ሥራችሁንም አሳምሩ፥ ልታገለግሉአቸውም ሌሎችን አማልክት አትከተሉ፥ ለእናንተና ለአባቶቻችሁም በሰጠሁት ምድር ትቀመጣላችሁ’ እያልሁ በማለዳ ተነሥቼ ባርያዎቼን ነቢያትን ሁሉ ላክሁባችሁ፤ ላክሁ፥ እናንተ ግን ጆሮአችሁን አላዘነበላችሁም እኔንም አልሰማችሁኝም።
ምናልባት የይሁዳ ቤት እኔ ላደርግባቸው ያሰብኩትን ክፉ ነገር ሁሉ ይሰሙ ይሆናል፥ ከዚህም የተነሣ ሁላቸውም ከክፉ መንገዳቸው ተመልሰው በደላቸውንና ኃጢአታቸውን ይቅር እል ይሆናል።”
ይህን የሚያስተውል ጠቢብ ሰው ማን ነው? እንዲያውጅስ የጌታ አፍ ለማን ተናገረ? ሰው እንዳያልፍባት ምድርስ ስለምን ጠፋች፥ እንደ ምድረ በዳስ ስለምን ተቃጠለች?
ምክንያቱም እኔ ያላሳዘንሁትን የጻድቁን ልብ በውሸት አሳዝናችኋልና፥ ከክፉ መንገዱ ተመልሶ በሕይወትም እንዳይኖር የኃጢአተኛውን እጅ አበርትታችኋልና፤
ስለዚህ የእስራኤል ቤት ሆይ፥ እያንዳንዱን ሰው እንደ መንገዱ እፈርዳለሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር። ተመለሱ፥ ኃጢአትም ዕንቅፋት እንዳይሆንባችሁ ከኃጢአታችሁ ሁሉ ተመለሱ።
የቀደሙት ነቢያት ለአባቶቻችሁ እንዲህ ብለው ሰብከዋል፦ “የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ ‘ከክፉ መንገዳችሁና ከክፉ ሥራችሁ ተመለሱ፤’” እነርሱ ግን አልሰሙም፤ እኔንም አላደመጡም፤ እንደ እነርሱ አትሁኑ፥ ይላል ጌታ።
የእውነት ትምህርት በአፉ ውስጥ ነበረ፥ በከንፈሩም ውስጥ ስሕተት አልተገኘም፤ ከእኔ ጋር በሰላምና በቅንነት ሄደ፥ ብዙዎችንም ከኃጢአት መለሰ።