ኤርምያስ 35:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)15 እንዲሁም፦ ‘እያንዳንዳችሁ ከክፉ መንገዳችሁ ተመለሱ፥ ሥራችሁንም አሳምሩ፥ ልታገለግሉአቸውም ሌሎችን አማልክት አትከተሉ፥ ለእናንተና ለአባቶቻችሁም በሰጠሁት ምድር ትቀመጣላችሁ’ እያልሁ በማለዳ ተነሥቼ ባርያዎቼን ነቢያትን ሁሉ ላክሁባችሁ፤ ላክሁ፥ እናንተ ግን ጆሮአችሁን አላዘነበላችሁም እኔንም አልሰማችሁኝም። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም15 አገልጋዮቼን ነቢያትን ሁሉ ደጋግሜ ወደ እናንተ ላክሁ፤ እነርሱም፣ “እያንዳንዳችሁ ከክፉ መንገዳችሁ ተመለሱ፤ ምግባራችሁን አስተካክሉ፤ ለእናንተና ለአባቶቻችሁ በሰጠኋቸው ምድር ትኖሩ ዘንድ ሌሎቹን አማልክት ለማገልገል አትከተሉ” አልኋችሁ። እናንተ ግን ጆሯችሁን ወደ እኔ አላዘነበላችሁም፤ አልሰማችሁኝምም። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም15 አገልጋዮቼ የሆኑትን ነቢያትን ወደ እናንተ ደጋግሜ ልኬአለሁ፤ እነርሱም ከክፉ ሥራችሁ ተመልሳችሁ ቅን የሆነውን ነገር እንድትሠሩ ነግረዋችኋል፤ ለባዕዳን አማልክት እንዳትሰግዱና የእነርሱም አገልጋዮች እንዳትሆኑ አስጠንቅቀዋችኋል፤ ለእናንተና ለቀድሞ አባቶቻችሁ በሰጠኋችሁ ምድር መኖር ትችሉ ዘንድ ይህን ሁሉ አዘዝኳችሁ፤ እናንተ ግን እኔን ለማዳመጥም ሆነ ለምነግራችሁ ቃል ትኲረት ልትሰጡት አልፈለጋችሁም። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)15 ደግሞም፦ እያንዳንዳችሁ ከክፉ መንገዳችሁ ተመለሱ፤ ሥራችሁንም አሳምሩ፤ ታገለግሉአቸውም ዘንድ ሌሎችን አማልክት አትከተሉ፤ ለእናንተና ለአባቶቻችሁም በሰጠሁት ምድር ትቀመጣላችሁ እያልሁ ባሪያዎችን ነቢያትን ሁሉ ልኬባችሁ ነበር፤ እናንተ ግን ጆሮአችሁን አላዘነበላችሁም፤ እኔንም አልሰማችሁኝም። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)15 ደግሞም፦ እያንዳንዳችሁ ከክፉ መንገዳችሁ ተመለሱ፥ ሥራችሁንም አሳምሩ፥ ታመልኩአቸውም ዘንድ ሌሎችን አማልክት አትከተሉ፥ ለእናንተና ለአባቶቻችሁም በሰጠሁት ምድር ትቀመጣላችሁ እያልሁ በማለዳ ተነሥቼ ባሪያዎቼን ነቢያትን ሁሉ ልኬባችሁ ነበር፥ እናንተ ግን ጆሮአችሁን አላዘነበላችሁም እኔንም አልሰማችሁኝም። Ver Capítulo |