Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሕዝቅኤል 18:30 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

30 ስለዚህ የእስራኤል ቤት ሆይ፥ እያንዳንዱን ሰው እንደ መንገዱ እፈርዳለሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር። ተመለሱ፥ ኃጢአትም ዕንቅፋት እንዳይሆንባችሁ ከኃጢአታችሁ ሁሉ ተመለሱ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

30 “የእስራኤል ቤት ሆይ፤ ስለዚህ እንደየሥራችሁ በእያንዳንዳችሁ ላይ እፈርዳለሁ፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር። እንግዲህ ንስሓ ግቡ፤ በኀጢአት እንዳትጠፉ፣ ከኀጢአታችሁ ሁሉ ተመለሱ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

30 “አሁንም እኔ ልዑል እግዚአብሔር ለእናንተ ለእስራኤላውያን የምላችሁ ይህ ነው፤ በክፉ ሥራችሁ እያንዳንዳችሁን እቀጣለሁ፤ ስለዚህ ከምታደርጉት ክፋት ተመለሱ፤ አለበለዚያ ኃጢአታችሁ ያጠፋችኋል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

30 የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሆይ! ስለ​ዚህ እንደ መን​ገዱ በየ​ሰዉ ሁሉ እፈ​ር​ድ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ንስሓ ግቡ፤ ኀጢ​አ​ትም ዕን​ቅ​ፋት እን​ዳ​ይ​ሆ​ን​ባ​ችሁ ከኀ​ጢ​አ​ታ​ችሁ ሁሉ ተመ​ለሱ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

30 የእስራኤል ቤት ሆይ፥ ስለዚህ እንደ መንገዱ በየሰዉ ሁሉ እፈርድባችኋለሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር ንስሐ ግቡ ኃጢአትም ዕንቅፋት እንዳይሆንባችሁ ከኃጢአታችሁ ሁሉ ተመለሱ።

Ver Capítulo Copiar




ሕዝቅኤል 18:30
44 Referencias Cruzadas  

ስለዚህ ለአባቶቻችሁ አምላክ ለጌታ ተናዘዙ፥ ፈቃዱንም አድርጉ፤ እራሳችሁንም ከምድሪቱ ሕዝቦችና ከእንግዶች ሴቶች ለዩ።”


እግዚአብሔር ሥራን ሁሉ የተሰወረውንም ነገር ሁሉ፥ መልካምም ቢሆን ክፉም ቢሆን፥ ወደ ፍርድ ያመጣዋልና።


እኔም በልቤ፦ ለማንኛውም ነገርና ለማንኛውም ሥራ ጊዜ አለውና በጻድቅና በክፉ ላይ እግዚአብሔር ይፈርዳል አልሁ።


ጉበኛውም፦ “ይነጋል ደግሞም ይመሻል፤ ትጠይቁ ዘንድ ብትወድዱ ጠይቁ፤ ተመልሳችሁም ኑ” አለ።


ለጽዮን ታዳጊ ይመጣል፥ በያዕቆብም ዘንድ ከኃጢአት ለሚርቁ፥ ይላል ጌታ።


እርሱም፦ ሁላችሁ እናንተ ከክፉ መንገዳችሁና ከሥራችሁ ክፋት ተመለሱ፤ ጌታም ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ለእናንተና ለአባቶቻችሁ በሰጣችሁ ምድር ተቀመጡ።


“ከዳተኞች ልጆች ሆይ! ተመለሱ፥ ከዳተኛነታችሁንም እፈውሳለሁ።” “እነሆ፥ አንተ አምላካችን ጌታ ነህና ወደ አንተ መጥተናል።


እንዲሁም፦ ‘እያንዳንዳችሁ ከክፉ መንገዳችሁ ተመለሱ፥ ሥራችሁንም አሳምሩ፥ ልታገለግሉአቸውም ሌሎችን አማልክት አትከተሉ፥ ለእናንተና ለአባቶቻችሁም በሰጠሁት ምድር ትቀመጣላችሁ’ እያልሁ በማለዳ ተነሥቼ ባርያዎቼን ነቢያትን ሁሉ ላክሁባችሁ፤ ላክሁ፥ እናንተ ግን ጆሮአችሁን አላዘነበላችሁም እኔንም አልሰማችሁኝም።


የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ መንገዳችሁንና ሥራችሁን አሳምሩ በዚህም ስፍራ እንድትቀመጡ አደርጋችኋለሁ።


ስለዚህ ለእስራኤል ቤት እንዲህ በል፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ተመለሱ፥ ከጣዖቶቻችሁም ተመለሱ፥ ከርኩሰቶቻችሁ ሁሉ ፊታችሁን መልሱ።


ክፉ ሰው ከሠራው ኃጢአት ሁሉ ቢመለስ፥ ትእዛዛቴንም ሁሉ ቢጠብቅ ፍትሕንና ጽድቅን ቢያደርግ፥ በእርግጥ በሕይወት ይኖራል እንጂ አይሞትም።


ሆኖም የእስራኤል ቤት የጌታ መንገድ ቀና አይደለም ይላሉ። የእስራኤል ቤት ሆይ፥ በውኑ መንገዶቼ ቀና አይደሉምን? ቀና ያልሆኑትስ የእናንተ መንገዶች አይደሉምን?


እኔ ጌታ ተናግሬአለሁ፤ ይፈፀማል፥ እኔም አደርገዋለሁ፤ አልቆጠብም፥ አልራራም፥ አልጸጸትም። እንደ መንገድሽና እንደ ሥራሽ ይፈርዱብሻል፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።


በሕያውነቴ እምላለሁ ኃጢአተኛው ሰው ከመንገዱ ተመልሶ በሕይወት እንዲኖር እንጂ ኃጢአተኛው እንዲሞት አልፈቅድም፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ የእስራኤል ቤት ሆይ ተመለሱ፥ ከክፉ መንገዳችሁ ተመለሱ፤ ስለ ምንስ ትሞታላችሁ? በላቸው።


እናንተ ግን፦ የጌታ መንገድ የቀና አይደለም ትላላችሁ። የእስራኤል ቤት ሆይ፥ በእያንዳንዳችሁ ላይ እንደ መንገዳችሁ እፈርድባችኋለሁ።


ነገር ግን ከመንገዱ እንዲመለስ ኃጢአተኛውን ሰው ብታስጠነቅቀው እርሱም ከመንገዱ ባይመለስ፥ በኃጢአቱ ይሞታል አንተ ግን ነፍስህን አድነሃል።


ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላቸዋል፦ እነሆ እኔ በወፈረ በግና በከሳ በግ መካከል እፈርዳለሁ።


ወደ መንግሥታት በተንኋቸው ወደ አገሮችም ተዘሩ፤ እንደ መንገዳቸውና እንደ ሥራቸው መጠን ፈረድሁባቸው።


አሁንም ዝሙታቸውንና የነገሥታቶቻቸውን ሬሳ ከእኔ ዘንድ ያርቁ፥ እኔም ለዘለዓለም በመካከላቸው እኖራለሁ።


ንጉሡ ያለቅሳል፥ ልዑሉም ውርደትን ይለብሳል፥ የምድሪቱም ሕዝቦች እጆች ይንቀጠቀጣሉ፥ እንደ መንገዳቸው መጠን አደርግባቸዋለሁ፥ እንደ ፍርዳቸውም መጠን እፈርድባቸዋለሁ፥ በዚያን ጊዜ እኔ ጌታ እንደሆንሁ ያውቃሉ።


አሁን ፍጻሜ በአንቺ ላይ ነው፥ ቁጣዬን በአንቺ ላይ እሰድዳለሁ፥ እንደ መንገድሽም እፈርድብሻለሁ፥ ርኩሰትሽንም ሁሉ እመልስብሻለሁ።


እርሱም የሠራዊት አምላክ ጌታ ነው፤ የመታሰቢያው ስም ጌታ ነው።


የቀደሙት ነቢያት ለአባቶቻችሁ እንዲህ ብለው ሰብከዋል፦ “የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ ‘ከክፉ መንገዳችሁና ከክፉ ሥራችሁ ተመለሱ፤’” እነርሱ ግን አልሰሙም፤ እኔንም አላደመጡም፤ እንደ እነርሱ አትሁኑ፥ ይላል ጌታ።


ተመልሳችሁም በጻድቁና በኃጢአተኛው መካከል፥ እግዚአብሔርን በሚያገለግለውና በማያገለግለው መካከል ያለውን ልዩነት ታያላችሁ።


የሰው ልጅ ከመላእክቱ ጋር በአባቱ ክብር ይመጣልና፤ በዚያን ጊዜ ለእያንዳንዱ እንደ ሥራው ይከፍለዋል።


አሕዛብ ሁሉ በፊቱ ይሰበሰባሉ፤ እረኛ በጎቹን ከፍየሎች እንደሚለይ እርስ በርሳቸው ይለያቸዋል፤


እንዲህም አለ፦ “መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ።”


እንግዲህ ለንስሐ የሚገባ ፍሬ አፍሩ፤


“አይደለም”፤ እላችኋለሁ፥ “ነገር ግን ንስሓ ባትገቡ ሁላችሁም እንዲሁ ትጠፋላችሁ።


ነገር ግን ንስሓ ባትገቡ ሁላችሁም እንደዚሁ ትጠፋላችሁ።”


ነገር ግን አስቀድሜ በደማስቆ ላሉት በኢየሩሳሌምም በይሁዳም አገር ሁሉ ለአሕዛብም ንስሓ ይገቡ ዘንድና ለንስሓ የሚገባ ነገር እያደረጉ ወደ እግዚአብሔር ይመለሱ ዘንድ ተናገርሁ።


ነገር ግን እንደ ጥንካሬህና ንስሓ እንደማይገባ ልብህ የእግዚአብሔር ቅን ፍርድ በሚገለጥበት በቁጣ ቀን በራስህ ላይ ቁጣን ታከማቻለህ።


ምኞት ከፀነሰች በኋላ ኃጢአትን ትወልዳለች፤ ኃጢአትም ካደገች በኋላ ሞትን ትወልዳለች።


ለሰው ፊትም ሳያደላ በእያንዳንዱ ላይ እንደ ሥራው የሚፈርደውን አባት ብላችሁ የምትጠሩት ከሆነ፥ በእንግድነታችሁ ዘመን በፍርሃት ኑሩ።


እንግዲህ ንስሓ ግባ፤ አለዚያ ፈጥኜ እመጣብሃለሁ፤ በአፌም ሰይፍ እዋጋቸዋለሁ።


እንግዲህ ከየት እንደ ወደቅህ አስብ፤ ንስሓም ግባ፥ የቀደመውንም ሥራህን አድርግ፤ አለዚያ እመጣብሃለሁ ንስሓም ባትገባ መቅረዝህን ከስፍራው እወስዳለሁ።


ሙታንን፥ እንዲሁም ታላላቆችንና ታናናሾችን በዙፋኑ ፊት ቆመው አየሁ፤ መጻሕፍትም ተከፈቱ፤ ሌላም መጽሐፍ ተከፈተ፤ እርሱም የሕይወት መጽሐፍ ነው፤ ሙታንም በመጻሕፍት በተጻፈው መሠረት፥ እንደ ሥራቸው መጠን ፍርድን ተቀበሉ።


“እነሆ በቶሎ እመጣለሁ፤ ለእያንዳንዱም እንደ ሥራው መጠን እከፍል ዘንድ ዋጋዬ ከእኔ ጋር አለ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos