ኤርምያስ 9:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)12 ይህን የሚያስተውል ጠቢብ ሰው ማን ነው? እንዲያውጅስ የጌታ አፍ ለማን ተናገረ? ሰው እንዳያልፍባት ምድርስ ስለምን ጠፋች፥ እንደ ምድረ በዳስ ስለምን ተቃጠለች? Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም12 ይህን መረዳት የሚችል ጥበበኛ ሰው ማን ነው? እግዚአብሔር ገልጾለት ይህንስ ማስረዳት የሚችል ማን ነው? ምድሪቱስ ሰው እንደማያልፍበት በረሓ ለምን ጠፋች? ለምን ወና ሆነች? Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም12 እኔም እንዲህ አልኩ፦ “ምድሪቱ ማንም ሊዘዋወርባት የማይችል ደረቅ በረሓና ጠፍ መሆንዋ ስለ ምንድን ነው? ይህንንስ የሚያስተውል ጥበበኛ ሰው ማን ነው? ለሌሎች ማስረዳት ይችል ዘንድ የገለጥክለትስ ማን ነው?” Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)12 ይህን የሚያስተውል ጠቢብ ሰው ማን ነው? ያወራስ ዘንድ የእግዚአብሔር አፍ ለማን ተናገረ? ሰው እንዳያልፍባት ምድርስ ስለ ምን ጠፋች፤ እንደ ምድረ በዳስ ስለ ምን ተቃጠለች? Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)12 ይህን የሚያስተውል ጠቢብ ሰው ማን ነው? ያወራስ ዘንድ የእግዚአብሔር አፍ ለማን ተናገረ? ሰው እንዳያልፍባት ምድርስ ስለምን ጠፋች፥ እንደ ምድረ በዳስ ስለ ምን ተቃጠለች? Ver Capítulo |