ኤርምያስ 21:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንደ ሥራችሁም ፍሬ እቀጣችኋለሁ፥ ይላል ጌታ፤ በጫካዋም ውስጥ እሳትን አነድዳለሁ፥ በዙሪያዋም ያለውን ሁሉ ይበላል።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንደ ሥራችሁ መጠን እቀጣችኋለሁ፤ ይላል እግዚአብሔር፤ በዱሯም እሳት እለኵሳለሁ፤ በዙሪያዋ ያለውንም ሁሉ ይበላል።’ ” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን ስላደረግሽው ነገር ሁሉ እኔ እቀጣሻለሁ፤ ቤተ መንግሥትሽ በእሳት እንዲቃጠል አደርጋለሁ፤ ያም እሳት በዙሪያው የሚገኘውን ነገር ሁሉ ያጋያል፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንደ ሥራችሁም ፍሬ እቀጣችኋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር በዱርዋም ውስጥ እሳትን አነድዳለሁ፤ በዙሪያዋም ያለውን ሁሉ ይበላል።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንደ ሥራችሁም ፍሬ እቀጣችኋለሁ፥ በዱርዋም ውስጥ እሳትን አነድዳለሁ፥ በዙሪያዋም ያለውን ሁሉ ይበላል። |
ጌታ በጽዮን ተራራና በኢየሩሳሌም ላይ የሚያደርገውን ሁሉ ከፈጸመ በኋላ፤ እንዲህ ይላል የአሦርን ንጉሥ ስለ ልቡ ትዕቢትና ስለ ንቀት አመለካከቱ እቀጣዋለሁ፤
ስለዚህ ጌታ፤ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤ በፈረጠሙ ጦረኞቹ ላይ የሚያከሳ በሽታ ይልካል፤ ከክብሩም በታች እንደ ነበልባል የሚንቦገቦግ እሳት ይለኰሳል።
አንተም እንዲህ አለክ፦ በሠረገላዬ ብዛት ወደ ተራሮች ከፍታ፥ ወደ ሲባኖስ ጥግ ወጥቻለሁ፤ ረጃጅሞቹን ዝግባዎች፥ የተመረጡትን ጥንዶች እቈርጣለሁ፥ ወደ ከፍታውም ዳርቻ ወደ ቀርሜሎስ ዱር እገባለሁ፤
ጌታ ስምሽን፦ “በመልካም ፍሬ የተዋበች የለመለመች የወይራ ዛፍ” ብሎ ጠራው፤ በጽኑ ዐውሎ ነፋስ ጩኸት እሳትን አነደደባት፥ ቅርንጫፎችዋም ተሰብረዋል።
ነገር ግን የሰንበትን ቀን እንድትቀድሱ፥ በሰንበትም ቀን ሸክምን ተሸክማችሁ በኢየሩሳሌም በሮች እንዳትገቡ የነገርኋችሁን ባትሰሙኝ፥ በበሮችዋ ላይ እሳትን አነድዳለሁ፥ የኢየሩሳሌምንም የንጉሥ ቅጥሮች ትበላለች፥ አትጠፋምም።’ ”
ጋሜል። በጽኑ ቁጣው የእስራኤልን ቀንድ ሁሉ ቀጠቀጠ፥ ቀኝ እጁን ከጠላት ፊት ወደ ኋላ መለሰ፥ በዙሪያውም እንደሚባላ እንደ እሳት ነበልባል ያዕቆብን አቃጠለ።
ለእስራኤልም ምድር እንዲህ ብለህ ተናገር፦ ጌታ እንዲህ ይላል፦ እነሆ በአንቺ ላይ ነኝ፥ ሰይፌን ከሰገባው እመዝዘዋለሁ፥ ጻድቁንና ክፉውን ከአንቺ ዘንድ አስወግዳለሁ።