ራሳቸው የሚሰጡትም መልስ ‘የእስራኤል ሕዝብ የቀድሞ አባቶቻቸውን ከግብጽ ምድር ያወጣ ጌታ አምላካቸውን በመተዋቸው ምክንያት ነው፤ ከዚህም በቀር ለእግዚአብሔር የነበራቸውን ታማኝነት ትተው ሌሎችን አማልክት አመለኩ፤ ሰገዱላቸውም፤ እግዚአብሔር ይህን ሁሉ የጥፋት መቅሠፍት ያመጣባቸውም ስለዚህ ነው’ የሚል ነው።”
ኤርምያስ 16:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንተም እንዲህ ትላቸዋለህ፦ ‘አባቶቻችሁ እኔን ስለ ተው ነው፥ ይላል ጌታ፥ ሌሎችንም አማልክት ተከተሉ አገለገሉአቸውም ሰገዱላቸውም፥ እነርሱም ትተውኛል፥ ሕጌንም አልጠበቁም፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲህ ትላቸዋለህ፤ ‘አባቶቻችሁ እኔን ስለ ተዉኝ ነው’ ይላል እግዚአብሔር፤ ‘ሌሎችን አማልክት በመከተል፣ ስላገለገሏቸውና ስላመለኳቸው ነው፤ ትተውኝ ኰበለሉ፤ ሕጌንም አልጠበቁም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያን ጊዜ እግዚአብሔር እንዲህ ይላችኋል በላቸው፦ ‘የቀድሞ አባቶቻችሁ ከእኔ ተለይተው የሐሰት አማልክትን በማምለክ አገለገሉ፤ እኔን ተዉኝ፤ ሕጌንም አልፈጸሙም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንተ እንዲህ ትላቸዋለህ፦ አባቶቻችሁ እኔን ስለ ተዉ ነው፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ሌሎችንም አማልክት ተከተሉ፤ አመለኩአቸውም፤ ሰገዱላቸውም፤ እነርሱም ትተውኛል፤ ሕጌንም አልጠበቁም፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንተ እንዲህ ትላቸዋለህ፦ አባቶቻችሁ እኔን ስለ ተው ነው፥ ይላል እግዚአብሔር፥ ሌሎችንም አማልክት ተከተሉ አመለኩአቸውም ሰገዱላቸውም፥ እነርሱም ትተውኛል፥ ሕጌንም አልጠበቁም፥ |
ራሳቸው የሚሰጡትም መልስ ‘የእስራኤል ሕዝብ የቀድሞ አባቶቻቸውን ከግብጽ ምድር ያወጣ ጌታ አምላካቸውን በመተዋቸው ምክንያት ነው፤ ከዚህም በቀር ለእግዚአብሔር የነበራቸውን ታማኝነት ትተው ሌሎችን አማልክት አመለኩ፤ ሰገዱላቸውም፤ እግዚአብሔር ይህን ሁሉ የጥፋት መቅሠፍት ያመጣባቸውም ስለዚህ ነው’ የሚል ነው።”
መልሰውም እንዲህ ይላሉ፦ ‘ከግብጽ ምድር ያወጣቸውን የአባቶቻቸውን አምላክ ጌታን ትተው ሌሎችን አማልክት ስለ ተከተሉ፥ ስለ ሰገዱላቸውም፥ ስለ አመለኩአቸውም፥ ስለዚህ ይህን ክፉ ነገር ሁሉ አመጣባቸው።’ ”
ካህናቱም፦ ‘ጌታ ወዴት አለ?’ አላሉም፥ የሕግ አዋቂዎች አላወቁኝም፤ ገዢዎችም ዐመፁብኝ፥ ነቢያትም በበዓል ትንቢት ተናገሩ፥ የማይረባውንም ነገር ተከተሉ።
ይህም የሆነው ስለ ሠሩት ክፋት እኔን ስላስቈጡኝ፥ በዚህም እናንተም አባቶቻችሁም እነርሱም ለማያውቁአቸው ለሌሎች አማልክት ለማጠንና ለማገልገል ስለ ሄዱ ነው።
በወደዱአቸውና ባገለገሉአቸው፥ በተከተሉአቸውና በፈለጉአቸው፥ በሰገዱላቸውም በፀሐይና በጨረቃ በሰማይም ሠራዊት ሁሉ ፊት ይዘረጉአቸዋል፤ አይሰበሰቡም አይቀበሩምም፥ በምድርም ፊት ላይ እንደ ጉድፍ ይሆናሉ።
ጌታ እንዲህ ይላል፦ “የጌታን ሕግ ጥለዋልና፥ ትእዛዙንም አልጠበቁምና፥ አባቶቻቸውም የተከተሉአቸው ሐሰቶቻቸው አስተዋቸዋልና ስለ ሦስት የይሁዳ ኃጢአት ስለ አራትም መቅሠፍቴን ከማድረግ አልመለስም።
ከአባቶቻችሁ ዘመን ጀምሮ ከትእዛዜ ርቃችኋል፥ አልጠበቃችሁትምም። ወደ እኔ ተመለሱ፥ እኔም ወደ እናንተ እመለሳለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ። እናንተ ግን፦ የምንመለሰው እንዴት ነው? ብላችኋል።
አሕዛብ እንደሚያደርጉት በመዳራት፥ በሥጋዊ ምኞት፥ በስካር፥ በመሶልሶል፥ ያለ ልክ በመጠጣት፥ በአስነዋሪ የጣዖት አምልኮ የተመላለሳችሁበት ያለፈው ዘመን ይበቃል።