ከዚህም የተነሣ ንጉሥ አካዝ ወደ አሦር ንጉሠ ነገሥት ወደ ቲግላት ፐሌሴር “እኔ ለአንተ ታማኝ አገልጋይህ ነኝ፤ ስለዚህም ወደ እኔ መጥተህ አደጋ ከጣሉብኝ ከሶርያና ከእስራኤል ነገሥታት እጅ አድነኝ” የሚል ጥያቄ የያዙ መልእክተኞች ላከ።
ኤርምያስ 13:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወዳጆችሽ እንዲሆኑ ያስተማርሻቸውን በራስሽ ላይ አለቆች ባደረጋቸው ጊዜ ምን ትያለሽ? እንደ ወላድ ሴት ምጥ አይዝሽምን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ልዩ ወዳጆች እንዲሆኑሽ ያስተማርሻቸው፣ ባለሥልጣን ሲሆኑብሽ ምን ትያለሽ? እንደምትወልድ ሴት፣ ምጥ አይዝሽምን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወዳጆች ብለሽ ያቀረብሻቸው ወራሪዎችሽና ገዢዎችሽ ሲሆኑ ምን ትያለሽ? በምጥ ላይ እንዳለች ሴት ሕመም አይሰማሽምን? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንቺ ትምህርት ያስተማርሻቸው አለቆችሽ ሆነው በጐበኙሽ ጊዜ ምን ትያለሽ? እንደ ወላድ ሴት ምጥ አይዝሽምን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወዳጆችሽ እንዲሆኑ ያስተማርሻቸውን በራስሽ ላይ አለቆች ባደረጋቸው ጊዜ ምን ትያለሽ? እንደ ወላድ ሴት ምጥ አይዝሽምን? |
ከዚህም የተነሣ ንጉሥ አካዝ ወደ አሦር ንጉሠ ነገሥት ወደ ቲግላት ፐሌሴር “እኔ ለአንተ ታማኝ አገልጋይህ ነኝ፤ ስለዚህም ወደ እኔ መጥተህ አደጋ ከጣሉብኝ ከሶርያና ከእስራኤል ነገሥታት እጅ አድነኝ” የሚል ጥያቄ የያዙ መልእክተኞች ላከ።
በምትጎበኙበት ቀን ምን ይውጣችኋል? ጥፋት ከሩቅ ሲመጣስ ምን ትሆናላችሁ? ርዳታን ለማግኘትስ ወደ ማን ትሸሻላችሁ? ሀብታችሁንስ የት ታገኙታላችሁ?
ሽብር ይይዛቸዋል፤ ሥቃይና ጭንቀት ይደርስባቸዋል፤ ምጥ እንደ ያዛት ሴት ያምጣሉ፤ እርስ በርሳቸው በድንጋጤ ይተያያሉ፤ ፊታቸውም በፍርሀት ቀይ ይሆናል።
በባዶ እግርሽ ከመሄድ፥ ጉሮሮሽንም ከውኃ ጥም ከልክዪ፤ አንቺ ግን፦ ‘ተስፋ የለኝም፥ አይሆንም! እንግዶችን ወድጄአለሁና፥ እከተላቸዋለሁም’ አልሽ።
እነሆ፥ በይሁዳ ንጉሥ ቤት የቀሩትን ሴቶች ሁሉ ወደ ባቢሎን ንጉሥ አለቆች ያወጣሉ፤ እነዚያም ሴቶች፦ ‘ባለምዋሎችህ አሳስተውሃል አሸንፈውሃልም፤ አሁን ግን እግሮችህ በጭቃ ውስጥ ገብተዋል እነርሱም ከአንተ ወደ ኋላ ተመልሰዋል’ ይላሉ።
አንቺም የተደመሰስሽ ሆይ! ምን ታደርጊአለሽ? ቀይ በለበስሽ ጊዜ፥ በወርቅ አንባርም ባጌጥሽ ጊዜ፥ ዓይንሽንም በኩል ተኩለሽ በተቆነጀሽ ጊዜ፥ በከንቱ እራስሽን ታጌጫለሽ፤ ውሽሞችሽ አቃለሉሽ፥ ነፍስሽን ይሹአታል።
እንደታመመች የበኩርዋንም እንደምትወልድ ሴት የጭንቀት ድምፅ ሰምቻለሁና፤ የጽዮን ሴት ልጅ ድምፅ በድካም ታቃስታለች፥ እጆችዋንም በመዘርጋት፦ “በነፍሰ ገዳዮች ፊት ነፍሴ ዝላለችና ወዮልኝ!” አለች።
ነቢያት በሐሰት ትንቢት ይናገራሉ፥ ካህናትም በእነዚህ እጅ ይገዛሉ፥ ሕዝቤም እንዲህ ያለውን ነገር ወድደዋል፤ በፍጻሜውስ ምን ታደርጋላችሁ?
እነርሱም፦ “ሰላምና ደኅንነት ነው” በሚሉ ጊዜ ምጥ እንደ ያዛት እርጉዝ ሴት ድንገተኛ ጥፋት በእነርሱ ላይ ይመጣባቸዋል፤ ከቶም አያመልጡም።