ኤርምያስ 22:23 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)23 አንቺ በሊባኖስ የምትቀመጪ፥ በዝግባ ዛፍም ውስጥ ጎጆሽን የምትሠሪ ሆይ! ምጥ እንደ ያዛት ሴት ሕመም በያዘሽ ጊዜ እንዴት ታቃስቻለሽ!” Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም23 አንቺ፣ ‘በሊባኖስ’ ውስጥ የምትኖሪ፣ መኖሪያሽን በዝግባ ዛፍ የሠራሽ ሆይ፤ ምጥ እንደ ያዛት ሴት፣ መከራ በላይሽ ሲመጣ ጩኸትሽ እንዴት ይሆን! Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም23 አሁንማ ከሊባኖስ መጥቶ በተሠራ የሊባኖስ እንጨት ውስጥ በሰላም ዐርፋችሁ ትኖራላችሁ፤ ነገር ግን እንደ ወላድ ሴት የምጥ ጣዕር ሲይዛችሁ ምን ይበጃችሁ ይሆን? Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)23 አንቺ በሊባኖስ የምትቀመጪ፥ በዝግባ ዛፍም ውስጥ የምታለቅሺ ሆይ! ምጥ እንደ ያዛት ሴት ሕማም በያዘሽ ጊዜ እንዴት ትጨነቂያለሽ! Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)23 አንቺ በሊባኖስ የምትቀመጪ፥ በዝግባ ዛፍም ውስጥ ጎጆሽን የምትሠሪ ሆይ፥ ምጥ እንደ ያዛት ሴት ሕማም በያዘሽ ጊዜ እንዴት ታጓሪያለሽ! Ver Capítulo |