ኢሳይያስ 51:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጽድቄ ፈጥኖ ቀርቦአል፥ ማዳኔም ወጥቶአል፥ ክንዴም በአሕዛብ ላይ ይፈርዳል፤ ደሴቶች እኔን በመተማመን ይጠባበቃሉ፥ በክንዴም ይታመናሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጽድቄ በፍጥነት እየቀረበ፣ ማዳኔም እየደረሰ ነው፤ ክንዴም ለመንግሥታት ፍትሕን ያመጣል፤ ደሴቶች ወደ እኔ ይመለከታሉ፤ ክንዴንም በተስፋ ይጠብቃሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ፈጥኜ በመምጣት አድናቸዋለሁ፤ በቅጽበት ድል የምነሣበት ጊዜ ይመጣል፤ በኀይሌ ሕዝቦችን ሁሉ እገዛለሁ፤ በደሴቶች የሚኖሩ ሕዝቦች፥ እኔን በተስፋ ይጠባበቃሉ፤ ኀይሌንም ተስፋ ያደርጋሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጽድቄ ፈጥና ትመጣለች፤ ማዳኔም እንደ ብርሃን ትደርሳለች፤ አሕዛብ በክንዴ ይታመናሉ፤ ደሴቶች እኔን ተስፋ ያደርጋሉ፤ በክንዴም ይታመናሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጽድቄ ፈጥኖ ቀርቦአል፥ ማዳኔም ወጥቶአል፥ ክንዴም በአሕዛብ ላይ ይፈርዳል፥ ደሴቶች እኔን በመተማመን ይጠባበቃሉ፥ በክንዴም ይታመናሉ። |
በዚያን ቀን፤ ጌታ እጁን ዘርግቶ እንደገና የተረፈውን የሕዝቡን ትሩፍ ከአሦር፤ ከታችኛው ግብጽ፤ ከላይኛው ግብጽ፤ ከኢትዮጵያ፤ ከኤላም፤ ከባቢሎን፤ ከሐማትና ከባሕር ጠረፍ ምድር ይሰበስባል።
በአንቺ ላይ የተሠራ መሣሪያ ሁሉ አይከናወንም፤ በፍርድም የሚነሣብሽን ምላስ ሁሉ ትፈርጂበታለሽ። የጌታ አገልጋዮች ርስት ይህ ነው፥ ጽድቃቸውም ከእኔ ዘንድ ነው፥ ይላል ጌታ።
እርሱ አክብሮሻልና ለአምላክሽ ለጌታ ስምና ለእስራኤል ቅዱስ ልጆችሽን ከሩቅ፥ ከእነርሱ ጋርም ብራቸውንና ወርቃቸውን ለማምጣት፥ ደሴቶች የተርሴስ መርከቦችም አስቀድመው ይጠባበቁኛል።
እነሆ፥ ጌታ ለምድር ዳርቻ አዋጅ እንዲህ ብሎ ነግሮአል፦ ለጽዮን ልጅ፦ “እነሆ፥ መድኃኒትሽ ይመጣል፤ እነሆ፥ ዋጋው ከእርሱ ጋር፥ ሥራውም በፊቱ አለ” በሏት።
ጌታ በእነርሱ ዘንድ የተፈራ ይሆናል፥ የምድርን አማልክት ሁሉ ያጠፋቸዋልና፤ የሕዝቦችም ደሴቶች ሁሉ ላይ የሚኖሩ ሰዎች፥ ሁሉም በያሉበት ሆነው ለእርሱ ይሰግዳሉ።
ቀንቀጥሮአልና፤ በዚያም ቀን ባዘጋጀው ሰው እጅ በዓለሙ ላይ በጽድቅ ሊፈርድ አለው፤ ስለዚህም እርሱን ከሙታን በማስነሣቱ ሁሉን አረጋግጦአል።”
ጌታ! እርሱን የሚቃወሙ ይደቅቃሉ፥ ከሰማይም ያንጐደጉድባቸዋል፥ ጌታ እስከ ምድር ዳርቻ ይፈርዳል፥ ለንጉሡም ኃይል ይሰጣል፥ የመሢሑንም ቀንድ ከፍ ከፍ ያደርጋል።”