Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መዝሙር 96:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ይመጣልና፥ በምድር ላይ ሊፈርድ ይመጣልና፥ እርሱም ዓለምን በጽድቅ አሕዛብንም በቅንነት ይፈርዳል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 እርሱ ይመጣልና በእግዚአብሔር ፊት ይዘምራሉ፤ በምድር ላይ ሊፈርድ ይመጣል፤ በዓለም ላይ በጽድቅ፣ በሕዝቦችም ላይ በእውነት ይፈርዳል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 እርሱም በምድር ላይ ሊፈርድ ይመጣል፤ በዓለም ላይ በጽድቅ፥ በሰዎች ላይ በእውነተኛነቱ ይፈርዳል።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 96:13
16 Referencias Cruzadas  

ሰማይም ተከፍቶ አየሁ፤ እነሆም ነጭ ፈረስ፤ የተቀመጠበትም የታመነና እውነተኛ ይባላል፤ በጽድቅም ይፈርዳል፤ ይዋጋልም።


ከእንግዲህም ወዲህ ጻድቅ ፈራጅ የሆነ ጌታ በዚያ ቀን ሊሸልመኝ የጽድቅ አክሊል አዘጋጅቶ ይጠብቀኛል፤ ደግሞም ለእኔ ብቻ ሳይሆን መገለጡን በፍቅር ለናፈቁት ሁሉ ነው።


እንዲሁም የተባረከውን ተስፋችንን እርሱም የታላቁን የአምላካችንንና የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር መገለጥ እንድንጠብቅ ያስተምረናል፤


ዓለምንም በጽድቅ አሕዛብንም በቅንነት ይፈርዳል።


በአሕዛብ መካከል፦ “ጌታ ነገሠ” በሉ። እንዳይናወጥም ዓለሙን እርሱ አጸናው፥ አሕዛብንም በቅንነት ይፈርዳል።


አቤቱ፥ አሕዛብ ያመስግኑህ፥ አሕዛብ ሁሉ ያመስግኑህ።


እንዲሀም አለኝ፦ “ዘመኑ ቀርቦአልና የዚህን መጽሐፍ ትንቢት ቃል በማኅተም አትዝጋው።


አሕዛብም ተቈጡ፤ ቁጣህም መጣ፤ በሙታንም የምትፈርድበት ዘመን መጣ፤ ለባርያዎችህም ለነቢያትና ለቅዱሳን፥ ስምህንም ለሚፈሩት ለታናናሾችና ለታላላቆችም ዋጋቸውን የምትሰጥበት ምድርንም የሚያጠፉትን የምታጠፋበት ዘመን መጣ።”


ይህም የሚሆነው ምስክርነታችን በእናንተ በመታመኑ የተነሣ ባመኑት ሁሉ ዘንድ ሊደነቅና፥ በቅዱሳኑም ሊከብር በሚመጣበት ጊዜ በዚያ ቀን ነው።


ጌታ በሕዝቦች ላይ ይፈርዳል፥ አቤቱ፥ እንደጽድቄ ፍረድልኝ፥ እንደ የዋህነቴም ይሁንልኝ።


አምላካችን ይመጣል ዝምም አይልም፥ እሳት በፊቱ ይቃጠላል፥ በዙሪያውም ብዙ ዐውሎ ነፋስ አለ።


እርሱ በሕዝቦች መካከል ይፈርዳል፤ የብዙ ሰዎችን አለመግባባት ያስወግዳል። እነርሱም ሰይፋቸውን ቀጥቅጠው ማረሻ ጦራቸውንም ማጭድ ያደርጋሉ። ሕዝብ በሕዝብ ላይ ሰይፍ አያነሣም፤ ጦርነትንም ከእንግዲህ አይማሩም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios