ኢሳይያስ 31:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንደሚበር ወፍ እንደዚሁ የሠራዊት ጌታ ኢየሩሳሌምን ይጋርዳታል፤ ይከልላታል፤ ይታደጋታል፤ እንዲሁም ያድናታል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዐናት ላይ እንደሚያንዣብቡ ወፎች፣ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ኢየሩሳሌምን እንዲሁ ይጋርዳታል፤ ይከልላታል፤ ይታደጋታል፤ በላይዋ ያልፋል፤ ያድናታልም።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወፍ በጎጆዋ ላይ ክንፍዋን ዘርግታ በማንጃበብ ጫጩቶችዋን እንደምትጠብቅ፥ እኔ የሠራዊት አምላክ ኢየሩሳሌምን እጋርዳታለሁ፤ እጠብቃታለሁ፤ አድናታለሁ፤ ከችግር አወጣታለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንደሚበርር ወፍ እንዲሁ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ኢየሩሳሌምን ይጋርዳታል፤ ይከልላታልም፤ ይታደጋታል፤ አልፎም ያድናታል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንደሚበርር ወፍ እንዲሁ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ኢየሩሳሌምን ይጋርዳታል፥ ይከልላታል፥ ይታደጋታል፥ አልፎም ያድናታል። |
እንዲሁም ጌታ ሕዝቅያስንና በኢየሩሳሌም የሚኖሩትን ከአሦር ንጉሥ ከሰናክሬም እጅ ከጠላቶቻቸውም ሁሉ እጅ አዳናቸው፤ በዙሪያቸውም ካለው ሁሉ አሳረፋቸው።
እናንተም፦ ‘ለጌታ የፋሲካ መሥዋዕት ነው፥ በግብጽ በእስራኤል ልጆች ቤቶች ላይ አልፎ ግብፃዊያንን በመታ ጊዜ፥ ቤቶቻችንን ያዳነበት ነው’ ትሉአቸዋላችሁ።” ሕዝቡም ተጎነበሱ ሰገዱም።
ሰው እጁን ወደ ወፍ ጎጆ እንደሚሰድ፤ እኔም እንዲሁ እጄን ወደ መንግሥታት ሀብት ሰደድሁ፤ ሰዎች የተተወ ዕንቁላል እንደሚሰበስቡ፤ እኔም እንዲሁ ምድርን ሁሉ ሰበሰብሁ፤ ክንፉን ያራገበ የለም፤ አፉንም ከፍቶ የጮኸ አልነበረም።’”
ጌታም በእነርሱ ላይ ይገለጣል፥ የአምላኩም ቀስት እንደ መብረቅ ይወጣል፤ እግዚአብሔር ጌታም መለከትን ይነፋል፥ ከደቡብም ዐውሎ ነፋስ ይመጣል።
አሁንም በዓይኔ ስቃያቸውን አይቻለሁና ከዚህ በኋላ ጨቋኝ አይመጣባቸውም፤ በቤቴ ዙሪያ እንደ ጠባቂ ጦር ሆኖ ከዘራፊዎች የሚጠብቅ እንዲሰፍር አደርጋለሁ።