Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢሳይያስ 31:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ጌታም እንዲህ ይለኛልና፦ አንበሳ ወይም የአንበሳ ደቦል በንጥቂያው ላይ ሲያገሣ፥ ብዙ እረኞች ቢከማቹበት ከቃላቸው እንደማይፈራ ከድምፃቸውም እንደማይዋረድ፥ እንደዚሁም የሠራዊት ጌታ በጽዮን ተራራና በኮረብታዋ ላይ ለመዋጋት ይወርዳል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 እግዚአብሔር እንዲህ ብሎኛል፤ “አንበሳ ወይም የአንበሳ ደቦል የሰበረውን ይዞ ሲያገሣ፣ ብዙ እረኞች ተጠራርተው ሲመጡበት፣ ጩኸታቸው እንደማያስፈራው፣ በድምፃቸውም እንደማይታወክ፣ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ በጽዮን ተራራና በከፍታዎቿ ላይ ለውጊያ እንዲሁ ይወርዳል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፦ “አንበሳ በገደለው እንስሳ ላይ በሚያገሣበት ጊዜ እረኞች ተጠራርተው የቱንም ያኽል ቢጮኹ የእነርሱ ጩኸት ምንም እንደማያስፈራው እኔም የሠራዊት አምላክ የጽዮንን ተራራና ኰረብቶቿን ለመከላከል የሚያግደኝ የለም።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይለ​ኛ​ልና፥ “አን​በሳ ወይም የአ​ን​በሳ ደቦል በን​ጥ​ቂ​ያው ላይ እን​ደ​ሚ​ያ​ገሣ፥ ድም​ፁም ተራ​ሮ​ችን እስ​ኪ​ሞላ በእ​ርሱ ላይ እን​ደ​ሚ​ጮህ፥ እረ​ኞ​ችም ሁሉ ሲጮ​ሁ​በት ከብ​ዛ​ታ​ቸው የተ​ነሣ እን​ደ​ማ​ይ​ፈራ፥ ከድ​ም​ፃ​ቸ​ውም የተ​ነሣ እን​ደ​ማ​ይ​ደ​ነ​ግጥ፥ እነ​ር​ሱም ከቍ​ጣው ብዛት የተ​ነሣ ድል እን​ደ​ሚ​ሆ​ኑና እን​ደ​ሚ​ደ​ነ​ግጡ፥ እን​ዲሁ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጽ​ዮን ተራ​ራና በኮ​ረ​ብ​ታዋ ላይ ይዋጋ ዘንድ ይወ​ር​ዳል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 እግዚአብሔርም እንዲህ ይለኛልና፦ አንበሳ ወይም የአንበሳ ደቦል በንጥቂያው ላይ ሲያገሣ፥ ብዙ እረኞች ቢከማቹበት ከቃላቸው እንደማይፈራ ከድምፃቸውም እንደማይዋረድ፥ እንዱሁ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በጽዮን ተራራና በኮረብታዋ ላይ ይዋጋ ዘንድ ይወርዳል።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 31:4
21 Referencias Cruzadas  

እንዲህም አለ፦ “ይሁዳ ሁሉ፥ በኢየሩሳሌም የምትኖሩ፥ አንተም ንጉሡ ኢዮሣፍጥ፥ ስሙ፤ ጌታ እንዲህ ይላችኋል፦ ‘ውግያው የጌታ ነው እንጂ የእናንተ አይደለምና ከዚህ ታላቅ ወገን የተነሣ አትፍሩ፥ አትደንግጡም።


ጌታ ስለ እናንተ ይዋጋል፥ እናንተም ዝም ትላላችሁ።”


የሰረገሎቹንም ጎማ አሰረ፥ ወደ ጭንቅም አስገባቸው፤ ግብፃውያንም፦ “ጌታ ግብፃውያንን ይዋጋላቸዋልና ከእስራኤል ፊት እንሽሽ” አሉ።


ስለዚህ ጌታ፤ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤ በፈረጠሙ ጦረኞቹ ላይ የሚያከሳ በሽታ ይልካል፤ ከክብሩም በታች እንደ ነበልባል የሚንቦገቦግ እሳት ይለኰሳል።


የጽዮን ሕዝብ ሆይ፤ እልል በሉ፤ በደስታም ዘምሩ፤ በመካከላችሁ ያለው የእስራኤል ቅዱስ ታላቅ ነውና።”


ጌታም ክቡር ድምፁን ያሰማል፥ የክንዱንም መውረድ በሚነድ ቁጣውና በምትበላ እሳት ነበልባል፥ በዐውሎ ነፋስም፥ በወጨፎም፥ በበረዶ፥ ጠጠርም ይገልጣል።


ጌታ በላዩ የሚወርድበት የታዘዘበት የበትር ድብደባ ሁሉ በከበሮና በመሰንቆ የታጀበ ይሆናል፤ በጦርነትም ክንዱን አንሥቶ ይዋጋቸዋል።


ጌታ እንደ ኃያል ይወጣል እንደ ሰልፈኛም ቅንዓትን ያስነሣል፤ ይጮኻል ድምፁንም ያሰማል በጠላቶቹም ላይ ይበረታል።


እነሆ፥ በጽኑ የበጎች በረት ላይ ከዮርዳኖስ ዱር ውስጥ እንደሚወጣ አንበሳ እንዲሁ እኔ ከእርሷ ዘንድ በድንገት አባርራቸዋለሁ፤ የተመረጠውንም ማንኛውንም ሰው በእርሷ ላይ እሾመዋለሁ፤ እንደ እኔ ያለ ማን ነው? ወይስ እኔን እንድመጣ የሚጠራኝ ማን ነው? ወይስ በፊቴ የሚቆም እረኛ ማን ነው?


ጌታን ይከተላሉ፥ እርሱም እንደ አንበሳ ያገሣል፤ ባገሣም ጊዜ ልጆቹ እየተንቀጠቀጡ ከምዕራብ ይመጣሉ።


አንበሳው አገሣ፤ የማይፈራ ማን ነው? ጌታ እግዚአብሔር ተናገረ፤ ትንቢት የማይናገር ማን ነው?”


በዚያም ቀን ከእነርሱ መካከል ደካማው እንደ ዳዊት እንዲሆን፥ የዳዊትም ቤት በፊታቸው እንደ እግዚአብሔር መልአክ እንደ ጌታ እንዲሆን፥ ጌታ በኢየሩሳሌም ለሚኖሩት መከታ ይሆናቸዋል።


ጌታም ይወጣል፥ በጦርነትም ቀን እንደሚዋጋ ከእነዚያ አሕዛቦች ጋር ይዋጋል።


ዐይኖቼንም አነሣሁ፥ እነሆም፥ በእጁ የመለኪያ ገመድ የያዘ አንድ ሰውን አየሁ።


የሠራዊት ጌታ ይጠብቃቸዋል፤ እነርሱም ይውጧቸዋል፥ በድንጋይ ወንጭፍም ያሸንፋሉ፤ ይጠጧቸዋል፥ በወይን ጠጅ እንደ ሰከረ ሰው ይሞቃቸዋል፤ እንደ መሠዊያም ማዕዘኖች፥ እንደ ጥዋዎቹም የተሞሉ ይሆናሉ።


አሁንም በዓይኔ ስቃያቸውን አይቻለሁና ከዚህ በኋላ ጨቋኝ አይመጣባቸውም፤ በቤቴ ዙሪያ እንደ ጠባቂ ጦር ሆኖ ከዘራፊዎች የሚጠብቅ እንዲሰፍር አደርጋለሁ።


እንደሚያገሣም አንበሳ በታላቅ ድምፅ ጮኸ፤ በጮኸም ጊዜ ሰባቱ ነጐድጓዶች በየድምፃቸው ተናገሩ።


ከሽማግሌዎቹም አንዱ “አታልቅስ፤ እነሆ ከይሁዳ ነገድ የሆነው አንበሳ፥ እርሱም የዳዊት ሥር መጽሐፉን ይዘረጋ ዘንድ ሰባቱንም ማኅተም ይፈታ ዘንድ ድል ነሥቶአል፤” አለኝ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos