Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘካርያስ 9:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ጌታም በእነርሱ ላይ ይገለጣል፥ የአምላኩም ቀስት እንደ መብረቅ ይወጣል፤ እግዚአብሔር ጌታም መለከትን ይነፋል፥ ከደቡብም ዐውሎ ነፋስ ይመጣል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 እግዚአብሔር በእነርሱ ላይ ይገለጣል፤ ፍላጻውም እንደ መብረቅ ይወጣል፤ ጌታ እግዚአብሔር መለከት ይነፋል፤ በደቡብም ዐውሎ ንፋስ ውስጥ ይጓዛል፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 እግዚአብሔር ከሕዝቡ በላይ ይገለጣል፤ የእርሱም ፍላጻዎች እንደ መብረቅ ይወረወራሉ፤ እግዚአብሔር አምላክ የመለከት ድምፅ ያሰማል፤ ከደቡብ በኩል እንደሚመጣ ዐውሎ ነፋስ ያልፋል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 እግዚአብሔርም በእነርሱ ላይ ይገለጣል፥ ፍላጻውም እንደ መብረቅ ይወጣል፣ ጌታ እግዚአብሔርም መለከትን ይነፋል፥ በደቡብም ዐውሎ ነፋስ ይሄዳል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 እግዚአብሔርም በእነርሱ ላይ ይገለጣል፥ ፍላጻውም እንደ መብረቅ ይወጣል፥ ጌታ እግዚአብሔርም መለከትን ይነፋል፥ በደቡብም ዐውሎ ነፋስ ይሄዳል።

Ver Capítulo Copiar




ዘካርያስ 9:14
28 Referencias Cruzadas  

ጌታ ከሰማያት አንጐደጐደ፥ ልዑልም ቃሉን ሰጠ። በረዶና የእሳት ፍምም፤


እነሆ፥ ጌታ መዓቱን በቁጣ፥ ዘለፋውንም በእሳት ነበልባል ይመልስ ዘንድ ከእሳት ጋር ይመጣል፥ ሰረገሎቹም እንደ ዐውሎ ነፋስ ይሆናሉ።


ጌታም ይወጣል፥ በጦርነትም ቀን እንደሚዋጋ ከእነዚያ አሕዛቦች ጋር ይዋጋል።


ዐይኖቼንም አነሣሁ፥ እነሆም፥ በእጁ የመለኪያ ገመድ የያዘ አንድ ሰውን አየሁ።


በዚያም ቀን እንዲህ ይሆናል፤ ታላቅ መለከት ይነፋል፥ በአሦርም የጠፉ፥ በግብጽ ምድርም የተሰደዱ ይመጣሉ፤ በተቀደሰውም ተራራ በኢየሩሳሌም ለጌታ ይሰግዳሉ።


በባሕር አጠገብ ስላለው ስለ ምድረ በዳ የተነገረ ትንቢት። ዐውሎ ነፋስ ከደቡብ እንደሚወጣ፥ እንዲሁ ከሚያስፈራ አገር ከምድረበዳ ይወጣል።


አየሁም፤ እነሆም ነጭ ፈረስ ወጣ፤ በእርሱም ላይ የተቀመጠው ቀስት ነበረው፤ አክሊልም ተሰጠው፤ ድል እየነሣ፥ ድልም ለመንሣት ወጣ።


በቀስቶችህ ብርሃን፥ በጦርህ መብረቅ ፀዳል፥ ፀሐይና ጨረቃ በመኖሪያቸው ቀጥ ብለው ቆሙ።


ጌታም ክቡር ድምፁን ያሰማል፥ የክንዱንም መውረድ በሚነድ ቁጣውና በምትበላ እሳት ነበልባል፥ በዐውሎ ነፋስም፥ በወጨፎም፥ በበረዶ፥ ጠጠርም ይገልጣል።


እግዚአብሔርም እርሱ ራሱ እንደ ፈቀደ በምልክትና በድንቅ ነገር በልዩ ልዩ ተአምራትም፥ መንፈስ ቅዱስንም በማደል አብሮ መሰከረለት።


በምልክትና በድንቅ ሥራ ኃይል፥ በመንፈስ ቅዱስም ኃይል፥ ከኢየሩሳሌም ጀምሬ እስከ እልዋሪቆን ድረስ እየዞርሁ የክርስቶስን ወንጌል ፈጽሜ ሰብኬአለሁ።


ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ አስተምሩአቸው፤ እነሆ እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።”


በዚያም ቀን ከእነርሱ መካከል ደካማው እንደ ዳዊት እንዲሆን፥ የዳዊትም ቤት በፊታቸው እንደ እግዚአብሔር መልአክ እንደ ጌታ እንዲሆን፥ ጌታ በኢየሩሳሌም ለሚኖሩት መከታ ይሆናቸዋል።


እንደሚበር ወፍ እንደዚሁ የሠራዊት ጌታ ኢየሩሳሌምን ይጋርዳታል፤ ይከልላታል፤ ይታደጋታል፤ እንዲሁም ያድናታል።


እናንት በዓለም ውስጥ ያላችሁና በምድር የምትኖሩ ሕዝቦች ሆይ፥ ምልክት በተራሮች ላይ በሚወጣ ጊዜ ተመልከቱ! መለከትም በተነፋ ጊዜ ስሙ!


የእስራኤልም አምላክ ጌታ ለእስራኤል ስለ ተዋጋላቸው ኢያሱ እነዚህን ነገሥታት ሁሉ ምድራቸውንም በአንድ ጊዜ ያዘ።


መላእክቱን ከታላቅ መለከት ጋር ይልካቸዋል፤ የእርሱን ምርጦች ከሰማያት ዳርቻ እስከ ዳርቻው ከአራቱ ነፋሳት ይሰበስባሉ።


ደስታቸው የተደበቁ ችግረኞችን እንደሚውጥ የሆነውን፥ እኛን ሊበትኑ እንደ ዐውሎ ነፋስ የመጡትን፤ የጦረኛውን ራስ በገዛ ጦሩ ወጋህ፤


ከተሰወረ ማደሪያውም ዐውሎ ነፋስ፥ ከሰሜንም ብርድ ይወጣል።


ፍላጻውን ላከ በተናቸውም፥ መብረቆችን አበዛ አወካቸውም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios