ደግሞም ጌታን እያከበሩና እያመሰገኑ “ቸር ነውና፥ ለእስራኤልም ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና” እያሉ ዘመሩ። ሕዝቡ ሁሉ ጌታን እያመሰገኑ በታላቅ ድምፅ እልል አሉ፥ ይህም የጌታ ቤት ስለ ተመሠረተ ነው።
ኢሳይያስ 26:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያም ቀን ይህ መዝሙር በይሁዳ ምድር ይዘመራል፦ የጸናች ከተማ አለችን፤ ቅጥሯንና ምሽጓን ለደኅንነታችን አኑሮታል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያ ቀን ይህ መዝሙር በይሁዳ ምድር ይዘመራል፤ ብርቱ ከተማ አለችን፤ አምላካችን ቅጥሮቿንና ምሽጎቿን፣ ለድነት አድርጓል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያን ጊዜ በይሁዳ ምድር የሚከተለው መዝሙር ይዘመራል፦ ጠንካራ ከተማ አለን፤ እንደ ቅጥርና እንደ ምሽግ የጸና መዳኛም አድርጎላታል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያም ቀን ይህን ቅኔ በይሁዳ ምድር ይዘምራሉ፤ እነሆም፥ የጸናችና የምታድን፥ ቅጥርንና ምሽግንም የምታደርግ ከተማ አለችን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያም ቀን ይህ ቅኔ በይሁዳ ምድር ይዘመራል፦ የጸናች ከተማ አለችን፥ ለቅጥርና ለምሽግ መድኃኒትን ያኖርባታል። |
ደግሞም ጌታን እያከበሩና እያመሰገኑ “ቸር ነውና፥ ለእስራኤልም ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና” እያሉ ዘመሩ። ሕዝቡ ሁሉ ጌታን እያመሰገኑ በታላቅ ድምፅ እልል አሉ፥ ይህም የጌታ ቤት ስለ ተመሠረተ ነው።
አንተ በር ሆይ፥ ወዮ በል፥ አንቺም ከተማ ሆይ፥ ጩኺ፤ ፍልስጥኤም ሆይ፥ ሁላችሁም ቀልጣችኋል፤ ጢስ ከሰሜን ይመጣል ከጭፍራውም ተለይቶ የሚቀር የለም።
በዚያም ቀን፦ እነሆ፥ አምላካችን ይህ ነው፤ ተስፋ አድርገነዋል፥ ያድነንማል፤ ጌታ ይህ ነው፤ ጠብቀነዋል፤ በማዳኑ ደስ ይለናል፤ ሐሤትም እናደርጋለን፥ ይባላል።
እነሆ፥ ጌታ ለምድር ዳርቻ አዋጅ እንዲህ ብሎ ነግሮአል፦ ለጽዮን ልጅ፦ “እነሆ፥ መድኃኒትሽ ይመጣል፤ እነሆ፥ ዋጋው ከእርሱ ጋር፥ ሥራውም በፊቱ አለ” በሏት።
እርሱም፦ የሐሤት ድምፅና የደስታ ድምፅ፥ የሙሽራው ድምፅና የሙሽራይቱ ድምፅ፥ ወደ ጌታም ቤት፦ ‘ጌታ ቸር ነውና፥ ጽኑ ፍቅሩም ለዘለዓለም ነውና የሠራዊት ጌታን አመስግኑ!’ እያሉ የምስጋናን መሥዋዕት የሚያመጡ ሰዎች ድምፅ ነው። የምድሪቱን ምርኮ ቀድሞ እንደ ነበረ አድርጌ እመልሳለሁና፥ ይላል ጌታ።
እነሆ፥ በቤቱ ውጭ በዙሪያው ቅጥር ነበረ፥ በሰውዬውም እጅ ያለው የመለኪያው ዘንግ ርዝመት አንድ ክንድ ከስንዝር የሆነ ስድስት ክንድ ነበረ፤ ቅጥሩንም ለካ፥ ስፋቱ አንድ ዘንግ፥ ቁመቱም አንድ ዘንግ ነበር።