Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢሳይያስ 31:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 እንደሚበር ወፍ እንደዚሁ የሠራዊት ጌታ ኢየሩሳሌምን ይጋርዳታል፤ ይከልላታል፤ ይታደጋታል፤ እንዲሁም ያድናታል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 በዐናት ላይ እንደሚያንዣብቡ ወፎች፣ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ኢየሩሳሌምን እንዲሁ ይጋርዳታል፤ ይከልላታል፤ ይታደጋታል፤ በላይዋ ያልፋል፤ ያድናታልም።”

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 ወፍ በጎጆዋ ላይ ክንፍዋን ዘርግታ በማንጃበብ ጫጩቶችዋን እንደምትጠብቅ፥ እኔ የሠራዊት አምላክ ኢየሩሳሌምን እጋርዳታለሁ፤ እጠብቃታለሁ፤ አድናታለሁ፤ ከችግር አወጣታለሁ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 እን​ደ​ሚ​በ​ርር ወፍ እን​ዲሁ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን ይጋ​ር​ዳ​ታል፤ ይከ​ል​ላ​ታ​ልም፤ ይታ​ደ​ጋ​ታል፤ አል​ፎም ያድ​ና​ታል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 እንደሚበርር ወፍ እንዲሁ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ኢየሩሳሌምን ይጋርዳታል፥ ይከልላታል፥ ይታደጋታል፥ አልፎም ያድናታል።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 31:5
18 Referencias Cruzadas  

በላባዎቹ ይጋርድሃል፥ ከክንፎቹም በታች ትጠለላለህ፥ ታማኝነቱ እንደ ጋሻና እንደ ቅጥር ይከብብሃል።


ንስር ጎጆዋን ቆስቁሳ፥ በጫጩቶቿም ላይ እንደምትሰፍፍ፥ ክንፎቹን ዘርግቶ ይወስደዋል፥ በክንፎቹም ያዝለዋል።


አንተንና ይህችንም ከተማ ከአሦር ንጉሥ እጅ እታደጋለሁ፥ ይህችንም ከተማ እጋርዳታለሁ።


ስለ እኔም ስለ አገልጋዬም ዳዊት ይህችን ከተማ አድናታለሁ፥ እጋርዳታለሁም።”


ጌታ ይረዳቸዋል፥ ያድናቸዋልም፥ ከከፉዎችም እጅ ያወጣቸዋል፥ ያድናቸዋልም፥ በእርሱ ታምነዋልና።


ሰው እጁን ወደ ወፍ ጎጆ እንደሚሰድ፤ እኔም እንዲሁ እጄን ወደ መንግሥታት ሀብት ሰደድሁ፤ ሰዎች የተተወ ዕንቁላል እንደሚሰበስቡ፤ እኔም እንዲሁ ምድርን ሁሉ ሰበሰብሁ፤ ክንፉን ያራገበ የለም፤ አፉንም ከፍቶ የጮኸ አልነበረም።’”


የወንዝ ፈሳሾች የእግዚአብሔርን ከተማ ደስ ያሰኛሉ፥ ልዑል ማደሪያውን ቀደሰ።


በግብፃውያን ያደረግሁትን፥ በንስርም ክንፍ እንዴት እንደ ተሸከምኋችሁ፥ ወደ እኔም እንዳመጣኋችሁ አይታችኋል።


እናንተም፦ ‘ለጌታ የፋሲካ መሥዋዕት ነው፥ በግብጽ በእስራኤል ልጆች ቤቶች ላይ አልፎ ግብፃዊያንን በመታ ጊዜ፥ ቤቶቻችንን ያዳነበት ነው’ ትሉአቸዋላችሁ።” ሕዝቡም ተጎነበሱ ሰገዱም።


ምድርም ቅርጽ የሌላትና ባዶ ነበረች፤ ጨለማም በጥልቁ ላይ ነበረ፤ የእግዚአብሔርም መንፈስ በውኃ ላይ ሰፍፎ ነበር።


ስለ ራሴ ክብር እንዲሁም ለአገልጋዬ ለዳዊት ስለ ሰጠሁት የተስፋ ቃል ይህችን ከተማ እኔ ራሴ ተከላክዬ አድናታለሁ።”


እንዲሁም ጌታ ሕዝቅያስንና በኢየሩሳሌም የሚኖሩትን ከአሦር ንጉሥ ከሰናክሬም እጅ ከጠላቶቻቸውም ሁሉ እጅ አዳናቸው፤ በዙሪያቸውም ካለው ሁሉ አሳረፋቸው።


በዚያም ቀን ይህ መዝሙር በይሁዳ ምድር ይዘመራል፦ የጸናች ከተማ አለችን፤ ቅጥሯንና ምሽጓን ለደኅንነታችን አኑሮታል።


እኔ ጌታ ጠባቂው ነኝ፤ ሁልጊዜ ውሃ አጠጣዋለሁ፤ ማንም እንዳይጎዳው በሌሊትና በቀን እጠብቀዋለሁ።


ጌታም በእነርሱ ላይ ይገለጣል፥ የአምላኩም ቀስት እንደ መብረቅ ይወጣል፤ እግዚአብሔር ጌታም መለከትን ይነፋል፥ ከደቡብም ዐውሎ ነፋስ ይመጣል።


እግዚአሔር በመካከልዋ ነው አትናወጥም፥ እግዚአብሔርም ፈጥኖ ይረዳታል።


ፈሪ ልብ ላላቸው፦ “እነሆ፥ አምላካችሁ ለበቀል፥ ብድራት ለመመለስ ይመጣል፤ መጥቶም ያድናችኋልና በርቱ፥ አትፍሩ!” በሉአቸው።


አሁንም በዓይኔ ስቃያቸውን አይቻለሁና ከዚህ በኋላ ጨቋኝ አይመጣባቸውም፤ በቤቴ ዙሪያ እንደ ጠባቂ ጦር ሆኖ ከዘራፊዎች የሚጠብቅ እንዲሰፍር አደርጋለሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios