ኢሳይያስ 62:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)10 እለፉ፥ በበሮች በኩል እለፉ፤ የሕዝቡንም መንገድ ጥረጉ፤ አዘጋጁ፥ ጎዳናውን አዘጋጁ፥ ድንጋዮቹንም አስወግዱ፤ ለአሕዛብም ዓርማ አሳዩ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም10 ዕለፉ፤ በበሮቹ በኩል ዕለፉ፤ ለሕዝቡ መንገድ አዘጋጁ፤ አስተካክሉ፤ ጐዳናውን አስተካክሉ! ድንጋዩን አስወግዱ፤ ለመንግሥታትም ምልክት አሳዩ። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም10 በቅጥር በሩ በኩል ዕለፉ፤ ለሰዎች መንገዱን አዘጋጁ፤ አውራ ጐዳናውን ሥሩ፤ ድንጋዮችን አስወግዱ፤ አርማውንም ለሕዝቦች ከፍ አድርጉ።” Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)10 ሂዱና በበሬ ውስጥ ግቡ፤ ለሕዝቤም መንገድን ጥረጉ፤ ድንጋዮቹንም ከጎዳናው አስወግዱ፤ ለአሕዛብም አላማ ያዙ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)10 እለፉ፥ በበሮች በኩል እለፉ፥ የሕዝቡንም መንገድ ጥረጉ፥ አዘጋጁ፥ ጎዳናውን አዘጋጁ፥ ድንጋዮቹንም አስወግዱ፥ ለአሕዛብም ዓላማ አነሡ። Ver Capítulo |