በአባቶችህ ታሪክ መጽሐፍ ምርመራ ይደረግ በዚያም በታሪክ መጽሐፍ ይህች ከተማ ዓመፀኛ እንደ ሆነች፥ ነገሥታትንና አውራጃዎችንም እንደ ጐዳች፥ ከጥንቱም ሽፍትነት በእርሷ እንደ ተጀመረ ታገኛለህ፥ ታውቃለህም፤ ስለዚህም ይህች ከተማ ፈርሳ ነበር።
ዕዝራ 6:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚን ጊዜ ንጉሡ ዳርዮስ ትእዛዝ አስተላለፈ። በባቢሎን መዛግብት ባሉበት ቤተ መጻሕፍት ምርመራ ተደረገ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ንጉሥ ዳርዮስ በባቢሎን ግምጃ ቤት የተቀመጡት መዛግብት እንዲመረመሩ ትእዛዝ ሰጠ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በባቢሎን ቤተ መንግሥት የሚገኙ መዛግብት ሁሉ ይመረመሩ ዘንድ ንጉሠ ነገሥት ዳርዮስ ትእዛዝ አስተላለፈ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያ ጊዜም ንጉሡ ዳርዮስ በባቢሎን ቤተ መዛግብት ያሉ የታሪክ መጻሕፍት እንዲመረመሩ አዘዘ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያ ጊዜም ንጉሡ ዳርዮስ መዛግብት ባሉበት በባቢሎን ቤተ መጻሕፍት እንዲመረመር አዘዘ። |
በአባቶችህ ታሪክ መጽሐፍ ምርመራ ይደረግ በዚያም በታሪክ መጽሐፍ ይህች ከተማ ዓመፀኛ እንደ ሆነች፥ ነገሥታትንና አውራጃዎችንም እንደ ጐዳች፥ ከጥንቱም ሽፍትነት በእርሷ እንደ ተጀመረ ታገኛለህ፥ ታውቃለህም፤ ስለዚህም ይህች ከተማ ፈርሳ ነበር።
እኔም አዝዣለሁ፥ ተመረመረም፥ ይህችም ከተማ ከጥንት ጀምራ በነገሥታት ላይ ዓመፀኛ እንደ ነበረች፥ በእርሷም ዓመፅና ሽፍትነት እንደ ተደረገ ተገኘ።
“አሁንም ይህ ነገር በንጉሡ ዐይን መልካም ቢሆን ይህ የእግዚአብሔር ቤት በኢየሩሳሌም እንዲሠራ ከንጉሡ ከቂሮስ ታዝዞ እንደሆነ በባቢሎን ባለው በንጉሡ ቤተ መዛግብት ይመርመር፥ ስለዚህም ነገር ንጉሡ ፈቃዱን ይላክልን።”
ጌታ ደስ አሰኝቶአቸዋልና፥ የእስራኤልን አምላክ የእግዚአብሔርን ቤትም ለመሥራት እጃቸውን እንዲያጸኑ የአሦርን ንጉሥ ልብ ወደ እነርሱ መልሶአልና የቂጣውን በዓል ሰባት ቀን በደስታ አከበሩ።
ስለ ይሁዳም ንጉሥ ስለ ኢዮአቄም እንዲህ በል፦ ‘ጌታ እንዲህ ይላል፦ አንተ፦ “የባቢሎን ንጉሥ በእርግጥ ይመጣል ይህችንም አገር ያፈርሳታል፥ ከሰውና ከእንስሳም ባዶ ያደርጋታል በማለት ለምን ጻፍህበት?” ብለህ ይህን ክርታስ አቃጥለሃል።
ኤርምያስም ሌላ ክርታስ ወሰደ፥ ለኔርያም ልጅ ለጸሐፊው ለባሮክ ሰጠው፤ እርሱም የይሁዳ ንጉሥ ኢዮአቄም በእሳት ያቃጠለውን የመጽሐፉን ቃላት ሁሉ ኤርምያስ እየነገረው ጻፈበት፥ ደግሞም እንደ ቀድሞው ያለ ተመሳሳይ ብዙ ቃላት ተጨመረበት።