ኤርምያስ 36:29 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)29 ስለ ይሁዳም ንጉሥ ስለ ኢዮአቄም እንዲህ በል፦ ‘ጌታ እንዲህ ይላል፦ አንተ፦ “የባቢሎን ንጉሥ በእርግጥ ይመጣል ይህችንም አገር ያፈርሳታል፥ ከሰውና ከእንስሳም ባዶ ያደርጋታል በማለት ለምን ጻፍህበት?” ብለህ ይህን ክርታስ አቃጥለሃል። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም29 ለይሁዳ ንጉሥ ለኢዮአቄም እንዲህ ብለህ ንገረው፤ ‘እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “የባቢሎን ንጉሥ በርግጥ ይመጣል፤ ይህችን ምድር፣ በርሷም ላይ የሚኖሩትን ሰዎችንና እንስሳትን ያጠፋል በማለት የጻፍህበት ለምንድን ነው?” ብለህ ብራናውን አቃጥለሃል። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም29 ለንጉሡም እንዲህ ብዬ እንድነግረው አዘዘኝ፦ “እነሆ አንተ የብራናውን ጥቅል አቃጥለሃል፤ ‘የባቢሎን ንጉሥ መጥቶ ይህችን ምድርና በእርስዋ የሚኖሩትን ሕዝብ፥ እንዲሁም እንስሶችን ሁሉ እንደሚያጠፋ ትንቢት የተናገርከው ስለምንድን ነው?’ ብለህ ኤርምያስን ጠይቀኸዋል፤ Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)29 የይሁዳንም ንጉሥ ኢዮአቄምን እንዲህ በለው፦ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ አንተ፦ የባቢሎን ንጉሥ በርግጥ ይመጣል፤ ይችንም ሀገር ያፈርሳታል፤ ሰውና እንስሳም ያልቃሉ ብለህ ለምን ጻፍህበት? ብለህ ይህን ክርታስ አቃጥለሃል። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)29 የይሁዳንም ንጉሥ ኢዮአቄምን እንዲህ በለው፦ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ አንተ፦ የባቢሎን ንጉሥ በእርግጥ ይመጣል ይህችንም አገር ያፈርሳታል ከሰውና ከእንስሳም ባዶ ያደርጋታል ብለህ ለምን ጻፍህበት? ብለህ ይህን ክርታስ አቃጥለሃል። Ver Capítulo |