ዕዝራ 2:68 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከአባቶች ቤቶች አለቆች አንዳንዶች፥ በኢየሩሳሌም ወዳለው ወደ ጌታ ቤት በመጡ ጊዜ፥ ለእግዚአብሔር ቤት በስፍራው እንዲሠራ በፈቃዳቸው መባ ሰጡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በኢየሩሳሌም ወደሚገኘው ወደ እግዚአብሔር ቤት በደረሱ ጊዜ፣ አንዳንድ የቤተ ሰብ መሪዎች በቀድሞው ቦታ እንደ ገና ለሚሠራው የእግዚአብሔር ቤት በበጎ ፈቃድ ስጦታ አደረጉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነዚህም ምርኮኞች ተመልሰው በኢየሩሳሌም የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ወደነበረበት ስፍራ በደረሱ ጊዜ አንዳንድ የቤተሰብ መሪዎች ቀድሞ በነበረበት ቦታ ቤተ መቅደሱን እንደገና መልሶ ለመሥራት ይረዳ ዘንድ በበጎ ፈቃድ የሚቀርብ የመባ ስጦታ አበረከቱ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በኢየሩሳሌምም ወዳለው ወደ እግዚአብሔር ቤት በመጡ ጊዜ ከአባቶች ቤቶች አለቆች አያሌዎች ለእግዚአብሔር ቤት በስፍራው ይሠሩት ዘንድ በፈቃዳቸው ሰጡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በኢየሩሳሌምም ወዳለው ወደ እግዚአብሔር ቤት በመጡ ጊዜ ከአባቶች ቤቶች አለቆች አያሌዎች ለእግዚአብሔር ቤት በስፍራው ይሠራ ዘንድ በፈቃዳቸው ሰጡ። |
ሰሎሞንም ጌታ ለአባቱ ለዳዊት በተገለጠበት በሞሪያ ተራራ ዳዊት ባዘጋጀው ስፍራ በኢያቡሳዊው በኦርና አውድማ በኢየሩሳሌም የጌታን ቤት መሥራት ጀመረ።
ባርያዎች ነን፥ አምላካችን ግን በባርነታችን አልተወንም፥ የአምላካችንን ቤት እንድንሠራና ፍርስራሾቹን እንድንጠግን መታደስን ሊሰጠን፥ በይሁዳና በኢየሩሳሌምም ግንብ ሊሰጠን በፋርስ ነገሥታት ፊት ፅኑ ፍቅሩን በእኛ ላይ ዘረጋ።
ልቡ ያነሣሣውና መንፈሱ ለመስጠት ፈቃደኛ የሆነ ሰው ሁሉ ለመገናኛው ድንኳን ሥራና ለአገልግሎቱ ሁሉ ለተቀደሰውም ልብስ የሚሆን ለጌታ ስጦታ አመጡ።
ከእስራኤል ልጆች ልባቸው ያነሣሣቸው ወንዶችና ሴቶች ሁሉ ጌታ በሙሴ እጅ እንዲሠራ ላዘዘው ሥራ ሁሉ የሚሆን ስጦታ በፈቃዳቸው ለጌታ አመጡ።
የመቅደሱን ሥራ ለመሥራት የእስራኤል ልጆች ያመጡትን ስጦታ ሁሉ ከሙሴ ወሰዱ። እነዚያም በፈቃዳቸው የሚያቀርቡትን ስጦታ አሁንም ማለዳ ማለዳ ወደ እርሱ ያመጡ ነበር።