La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ሕዝቅኤል 44:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ወደ ምሥራቅ ወደሚመለከተው በውጭ ወዳለው ወደ መቅደሱ በር መለሰኝ፤ ተዘግቶም ነበር።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከዚያም ያ ሰው ለምሥራቅ ትይዩ ወደ ሆነው በስተ ውጩ ወዳለው ወደ መቅደሱ በር መልሶ አመጣኝ፤ ተዘግቶም ነበር።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ያም ሰው በስተ ምሥራቅ በኩል ወደሚገኘው ወደ ቤተ መቅደሱ ውጪ በር ወሰደኝ፤ በሩም ተዘግቶ ነበር፤

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ወደ ምሥ​ራ​ቅም ወደ​ሚ​መ​ለ​ከ​ተው በስተ ውጭ ወደ አለው ወደ መቅ​ደሱ በር መለ​ሰኝ፤ ተዘ​ግ​ቶም ነበር።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ወደ ምሥራቅም ወደሚመለከተው በስተ ውጭ ወዳለው ወደ መቅደሱ በር አመጣኝ፥ ተዘግቶም ነበር።

Ver Capítulo



ሕዝቅኤል 44:1
12 Referencias Cruzadas  

እስከ ዛሬም ድረስ በንጉሥ በር በምሥራቅ በኩል ሰፍረዋል፤ ለሌዊ ልጆች ሰፈር በርም ጠባቂዎች ነበሩ።


ኢዮሣፍጥም በይሁዳና በኢየሩሳሌም ጉባኤ መካከል በጌታ ቤት ውስጥ በአዲሱ አደባባይ ፊት ቆመ፤


በጌታም ቤት በሁለቱ አደባባዮች ላይ ለሰማይ ሠራዊት ሁሉ መሠዊያዎችን ሠራ።


እንዲሁም የካህናቱን አደባባይ፥ ታላቁንም አደባባይ፥ የአደባባዩንም ደጆች ሠራ፥ ደጆቻቸውንም በናስ ለበጠ።


ከዚያም ወደ ውጪው አደባባይ አመጣኝ፥ እነሆ በአደባባዩ ዙሪያ የተሠሩ ዕቃ ቤቶችና ወለል ነበሩ፤ በወለሉም ላይ ሠላሳ ዕቃ ቤቶች ነበሩ።


ፊቱ ወደ ምሥራቅ ወደሚመለከተው በር መጣ፥ በደረጃዎቹም ወጥቶ በበሩ በኩል ያለውን የቤቱን መግቢያ ወለል ወርዱን ለካ አንድ ዘንግ ነበር፥ የሌላኛውም የቤቱ መግቢያ ወለል ወርድ አንድ ዘንግ ነበር።


ካህናቱም ከገቡ በኋላ የሚያገለግሉበትን ልብስ ሳያወልቁ ከመቅደሱ ወደ ውጭው አደባባይ አይወጡም፥ የተቀደሱ ናቸውና፤ ወደ ሕዝቡ ቦታ ሲቀርቡ ሌላ ልብስ መልበስ አለባቸው።


ወደ ምሥራቅ ወደሚመለከተው በር አመጣኝ።


የጌታ ክብር በሩ ወደ ምሥራቅ ወደሚመለከተው ቤት ገባ።


ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በውስጠኛው አደባባይ ፊቱ ወደ ምሥራቅ የሚመለከተው በር በስድስቱ የሥራ ቀኖች ይዘጋ፤ ነገር ግን በሰንበት ቀን ይከፈት እንዲሁም በወር መባቻ ቀን ይከፈት።


መስፍኑ በፈቃዱ የሚያቀርበውን መሥዋዕት፥ የሚቃጠለውን መሥዋዕት፥ ወይም የሰላሙን መሥዋዕት፥ በፈቃዱ ለጌታ የሚያቀርበውን መሥዋዕት ባቀረበ ጊዜ፥ ወደ ምሥራቅ የሚመለከተው በር ይከፈትለት፥ በሰንበትም ቀን እንደሚያደርግ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የሰላሙን መሥዋዕት ያቅርብ፤ ከዚያ በኋላ ይውጣ፥ ከወጣም በኋላ በሩ ይዘጋ።