ሕዝቅኤል 46:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)12 መስፍኑ በፈቃዱ የሚያቀርበውን መሥዋዕት፥ የሚቃጠለውን መሥዋዕት፥ ወይም የሰላሙን መሥዋዕት፥ በፈቃዱ ለጌታ የሚያቀርበውን መሥዋዕት ባቀረበ ጊዜ፥ ወደ ምሥራቅ የሚመለከተው በር ይከፈትለት፥ በሰንበትም ቀን እንደሚያደርግ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የሰላሙን መሥዋዕት ያቅርብ፤ ከዚያ በኋላ ይውጣ፥ ከወጣም በኋላ በሩ ይዘጋ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም12 “ ‘ገዥው የበጎ ፈቃድ ስጦታ፣ የሚቃጠል መሥዋዕትም ሆነ የኅብረት መሥዋዕት ለእግዚአብሔር በሚያቀርብበት ጊዜ፣ በምሥራቅ ትይዩ የሆነው በር ይከፈትለት፤ በሰንበት ቀን እንደሚያደርገው ሁሉ የሚቃጠል መሥዋዕቱንም ሆነ የኅብረት መሥዋዕቱን ያቅርብ፤ ከዚያ በኋላ ይወጣል፤ በሩም ይዘጋል። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም12 “በሥልጣን ላይ ያለው መስፍን በሙሉ የሚቃጠልም ሆነ ወይም የደኅንነት መሥዋዕት በበጎ ፈቃደኛነት በግሉ ለእግዚአብሔር ማቅረብ ቢፈልግ ወደ ውስጠኛው አደባባይ የሚያስገባው የምሥራቁ በር ይከፈትለት፤ የመባውንም አቀራረብ በሰንበት ቀን በሚያደርገው ዐይነት ይፈጽም፤ እርሱም ወጥቶ ከሄደ በኋላ በሩ ይዘጋ።” Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)12 አለቃውም በፈቃዱ የሚያቀርበውን መሥዋዕት፥ የሚቃጠለውን መሥዋዕት፥ ወይም በፈቃዱ ለእግዚአብሔር የሚያቀርበውን የደኅንነቱን መሥዋዕት በአቀረበ ጊዜ፥ ወደ ምሥራቅ የሚመለከተው በር ይከፈትለት፤ በሰንበትም ቀን እንደሚያደርግ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የደኅንነቱን መሥዋዕት ያቅርብ፤ ከዚያም በኋላ ይውጣ፤ ከወጣም በኋላ በሩ ይዘጋ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)12 አለቃውም በፈቃዱ የሚያቀርበውን መሥዋዕት፥ የሚቃጠለውን መሥዋዕት፥ ወይም በፈቃዱ ለእግዚአብሔር የሚያቀርበውን የደኅንነቱን መሥዋዕት፥ ባቀረበ ጊዜ፥ ወደ ምሥራቅ የሚመለከተው በር ይከፈትለት፥ በሰንበትም ቀን እንደሚያደርግ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የደኅንነቱን መሥዋዕት ያቅርብ፥ ከዚያም በኋላ ይውጣ፥ ከወጣም በኋላ በሩ ይዘጋ። Ver Capítulo |