ሕዝቅኤል 40:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)6 ፊቱ ወደ ምሥራቅ ወደሚመለከተው በር መጣ፥ በደረጃዎቹም ወጥቶ በበሩ በኩል ያለውን የቤቱን መግቢያ ወለል ወርዱን ለካ አንድ ዘንግ ነበር፥ የሌላኛውም የቤቱ መግቢያ ወለል ወርድ አንድ ዘንግ ነበር። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም6 ከዚያም በምሥራቅ ትይዩ ወዳለው በር መጣ፤ ደረጃዎቹን ወጥቶ የበሩን መግቢያ መድረክ ለካ፤ ቁመቱም አንድ ዘንግ ነበር። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም6 ከዚያም በኋላ በስተምሥራቅ በኩል ወዳለው የቅጽር በር አልፎ ሄደ፤ ደረጃውንም ወጥቶ ከጫፉ የመድረኩን ወለል ሲለካ አንድ ዘንግ ሆነ፤ Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)6 ወደ ምሥራቅ ወደሚመለከተውም በር መጣ፤ በሰባቱም ደረጃዎች ላይ ወጣ፤ በበሩ በኩል ያለውንም የመድረኩን ወለል ወርዱን አንድ ዘንግ አድርጎ ለካ፤ የሁለተኛውም ወለል ወርድ አንድ ዘንግ ነበረ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)6 ወደ ምሥራቅ ወደሚመለከተውም በር መጣ በደረጃዎቹም ላይ ወጣ፥ በበሩ በኩል ያለውንም የመድረኩን ወለል ወርዱን አንድ ዘንግ አድርጎ ለካ። Ver Capítulo |