ሕዝቅኤል 40:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰውዬውም እንዲህ አለኝ፦ “የሰው ልጅ ሆይ፥ በዓይንህ እይ፥ በጆሮህም ስማ፥ የማሳይህን ሁሉ ልብ ብለህ አስተውል፥ ይህን እንዳሳይህ ወደዚህ ተመርተሃልና የምታየውንም ሁሉ ለእስራኤል ቤት ንገር።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰውየውም እንዲህ አለኝ፤ “የሰው ልጅ ሆይ፤ በዐይንህ እይ፤ በጆሮህ ስማ፤ የማሳይህንም ሁሉ ልብ ብለህ አስተውል፤ ወደዚህ የመጣኸው ለዚህ ነውና ያየኸውንም ሁሉ ለእስራኤል ቤት ንገር።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰውየውም እንዲህ አለኝ፦ “የሰው ልጅ ሆይ! እዚህ ድረስ እንድትመጣ የተደረገበት ምክንያት እኔ የማሳይህን ሁሉ እንድትረዳ ስለ ሆነ ልብ ብለህ ተመልከት፤ በጥንቃቄም ስማ፤ የምታየውንም ሁሉ ለእስራኤል ሕዝብ ንገራቸው።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያም ሰው፥ “የሰው ልጅ ሆይ! ይህን አሳይህ ዘንድ አንተ ወደዚህ መጥተሃልና በዐይንህ እይ፤ በጆሮህም ስማ፤ የማሳይህንም ሁሉ በልብህ ጠብቅ፤ የምታየውንም ሁሉ ለእስራኤል ቤት ንገር” አለኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰውዬውም፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ ይህን አሳይህ ዘንድ አንተ ወደዚህ ተመርተሃልና በዓይንህ እይ በጆሮህም ስማ በማሳይህም ሁሉ ላይ ልብህን አድርግ፥ የምታየውንም ሁሉ ለእስራኤል ቤት ንገር አለኝ። |
“ጌታ እንዲህ ይላል፦ በጌታ ቤት አደባባይ ቁም፥ በጌታም ቤት ውስጥ ለመስገድ ለሚመጡት ለይሁዳ ከተሞች ሁሉ እንድትናገራቸው ያዘዝሁህን ቃላት ሁሉ ተናገር፤ አንዲትም ቃል አትጉድል።
እርሱም እንዲህ አለኝ፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ ወደ እስራኤል ልጆች፥ ወደ ዓመፀኞች አገር፥ በእኔ ላይ ወደ ዐመፁት እልክሃለሁ። እነርሱና አባቶቻቸው እስከ ዛሬ ቀን ድረስ በእኔ ላይ ዐመፁ።
ጌታም እንዲህ አለኝ፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ ስለ ጌታ ቤት ሥርዓት ሁሉ እና ሕጉን ሁሉ የምናገርህን ሁሉ ልብ አድርግ በዓይንህ ተመልከት በጆሮህም ስማ፤ የቤቱን መግቢያ የመቅደሱንም መውጫ ሁሉ ልብ አድርግ።
እንዲህ አላቸው፦ “የዚህን ሕግ ቃላት በጥንቃቄ መጠበቅ ይችሉ ዘንድ ልጆቻችሁን እንድታዙ፥ እኔ ዛሬ በእናንተ ላይ ምስክር እንዲሆን የምሰጣችሁን ቃላት ሁሉ በልባችሁ አኑሩት።