ሕዝቅኤል 40:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)3 ወደዚያም አመጣኝ፥ እነሆ፥ መልኩ ናስ የመሰለ አንድ ሰው በዚያ ነበረ፥ በእጁም የተልባ እግር ገመድና የመለኪያ ዘንግ ይዞ ነበረ፤ እርሱም በበሩ አጠገብ ቆሞ ነበር። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም3 ወደዚያ ወሰደኝ፤ እነሆ መልኩ ናስ የሚመስል ሰው አየሁ፤ እርሱም የሐር ገመድና መለኪያ ዘንግ በእጁ ይዞ በመግቢያው በር ላይ ቆሞ ነበር። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም3 ወደዚያ ሲወስደኝም እንደ ነሐስ የሚያበራ መልክ ያለውን አንድ ሰው አየሁ፤ እርሱም ከበፍታ የተሠራ ገመድና መለኪያ ዘንግ ይዞ በቅጽሩ በር አጠገብ ቆሞ ነበር። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)3 ወደዚያም አመጣኝ፤ እነሆም መልኩ እንደሚያንፀባርቅ ናስ መልክ የመሰለ አንድ ሰው በዚያ ነበረ፤ በእጁም የተልባ እግር ገመድና የመለኪያ ዘንግ ነበረ፤ እርሱም በበሩ አጠገብ ቆሞ ነበር። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)3 ወደዚያም አመጣኝ፥ እነሆም፥ መልኩ እንደ ናስ መልክ የመሰለ አንድ ሰው በዚያ ነበረ፥ በእጁም የተልባ እግር ገመድና የመለኪያ ዘንግ ነበረ፥ እርሱም በበሩ አጠገብ ቆሞ ነበር። Ver Capítulo |