Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሕዝቅኤል 43:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 አንተም የሰው ልጅ ሆይ፥ በኃጢአታቸው እንዲያፍሩ ለእስራኤል ቤት ስለ ቤቱ ንገራቸው፥ ንድፉንም ይለኩ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 “የሰው ልጅ ሆይ፤ ስለ ኀጢአታቸው ያፍሩ ዘንድ፣ ለእስራኤል ሕዝብ ቤተ መቅደሱን አሳያቸው፤ ንድፉንም ያስተውሉ፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ቀጥሎም እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፦ “የሰው ልጅ ሆይ! ለእስራኤል ሕዝብ ስለ ቤተ መቅደሱ አሠራር ንገራቸው፤ ንድፉንም ያጥኑ፤ ኃጢአት የሞላበት ሥራቸውንም በማስታወስ እንዲያፍሩ አድርጋቸው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 “አን​ተም የሰው ልጅ ሆይ፥ ሥራ​ቸ​ው​ንና ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውን ይተዉ ዘንድ ለእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ይህን ቤት አሳ​ያ​ቸው፤ አም​ሳ​ያ​ው​ንም ይለኩ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 አንተም የሰው ልጅ፥ ከኃጢአታቸው የተነሣ ያፍሩ ዘንድ ለእስራኤል ወገን ይህን ቤት አሳያቸው አምሳያውንም ይለኩ።

Ver Capítulo Copiar




ሕዝቅኤል 43:10
12 Referencias Cruzadas  

ዳዊትም ለመቅደሱ ወለል፥ ለቤቱም፥ ለቤተ መዛግብቱም፥ ለደርቡና ለውስጡም ጓዳዎች፥ ለስርየቱም መክደኛ መቀመጫ ንድፈ ሐሳቡን ለልጁ ለሰሎሞን ሰጠው።


ዳዊትም፦ “የሥራውን ሁሉ ንድፈ ሐሳብ እንዳውቅ ይህ ሁሉ በጌታ እጅ ተጽፎ መጣልኝ” አለ።


በተራራው ላይ ባሳየሁህ ምሳሌ መሠረት ለመስራት ጥንቃቄ አድርግ።”


የአንቺ ታላቅና የአንቺ ታናሽ እኅቶችሽን በተቀበልሽ ጊዜ መንገድሽን ታስቢያለሽ ታፍሪያለሽም፥ ሴቶች ልጆች እንዲሆኑሽም ለአንቺ እሰጣቸዋለሁ፥ ከቃል ኪዳንሽ የተነሣ ግን አይደለም።


ያደረግሽውን ሁሉ ይቅር ባልሁሽ ጊዜ፥ እንድታስቢውና እንድታፍሪ፥ ከውርደትሽም የተነሣ ደግሞ አፍሽን እንዳትከፍቺ ነው፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።


የሰው ልጅ ሆይ፥ በጢሮስ ንጉሥ ላይ ሙሾ አሞሽተህ እንዲህ በለው፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጥበብን የተሞላህ ውበትህም የተፈጸመ መደምደሚያ አንተ ነህ።


ሰውዬውም እንዲህ አለኝ፦ “የሰው ልጅ ሆይ፥ በዓይንህ እይ፥ በጆሮህም ስማ፥ የማሳይህን ሁሉ ልብ ብለህ አስተውል፥ ይህን እንዳሳይህ ወደዚህ ተመርተሃልና የምታየውንም ሁሉ ለእስራኤል ቤት ንገር።”


በሠሩት ሥራ ሁሉ የሚያፍሩ ከሆነ፥ የቤቱን ንድፉንና አሠራሩን፥ መውጫውንና መግቢያውን፥ አጠቃላይ ንድፉን፥ ሥርዓቱን ሁሉ፥ ንድፉን ሁሉ፥ ሕጉን ሁሉ አሳውቃቸው፤ ንድፉን ሁሉና ሥርዓቱን ሁሉ እንዲያዩትና እንዲያደርጉትም በፊታቸው ጻፈው።


ጌታም እንዲህ አለኝ፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ ስለ ጌታ ቤት ሥርዓት ሁሉ እና ሕጉን ሁሉ የምናገርህን ሁሉ ልብ አድርግ በዓይንህ ተመልከት በጆሮህም ስማ፤ የቤቱን መግቢያ የመቅደሱንም መውጫ ሁሉ ልብ አድርግ።


ታዲያ አሁን ከምታፍሩበት ነገር ሌላ ያንጊዜ ምን ፍሬ ነበራችሁ? የእነዚህ ነገሮች መጨረሻ ሞት ነውና።


ስለዚህም እንዲህ አልን፦ በሚመጣው ዘመን ለእኛ ወይም ለትውልዳችን ይህን ሲሉ እኛ እንዲህ እንላለን፦ ‘እነሆ፥ አባቶቻችን የሠሩትን የጌታን መሠዊያ ምሳሌ እዩ፤ በእኛና በእናንተ መካከል ምስክር ነው እንጂ የሚቃጠል መሥዋዕትንና ሌላ መሥዋዕትን ለማቅረብ አይደለም።’


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos