ሕዝቅኤል 35:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሰው ልጅ ሆይ፥ ፊትህን ወደ ሴይር ተራራ አድርግ፥ ትንቢትም ተናገርበት፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “የሰው ልጅ ሆይ፤ ፊትህን ወደ ሴይር ተራራ አዙር፤ ትንቢትም ተናገርበት፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “የሰው ልጅ ሆይ! ፊትህን ወደ ኤዶም ተራራ መልሰህ በሕዝቡም ላይ ትንቢት ተናገር፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “የሰው ልጅ ሆይ! ፊትህን ወደ ሴይር ተራራ መልስ፤ ትንቢትም ተናገርበት፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሰው ልጅ ሆይ፥ ፊትህን ወደ ሴይር ተራራ አድርግ፥ ትንቢትም ተናገርበት፥ እንዲህም በለው፦ |
እንግዲህ አሁን፥ እነሆ፥ እስራኤል ከግብጽ ምድር በወጡ ጊዜ እንዳይወርሯቸው ያልፈቀድህላቸው፥ ነገር ግን ትተዋቸው ያላጠፉአቸው፥ የአሞንና የሞዓብ ልጆች የሴይርም ተራራ ሰዎች፥
ኤዶምያስ እና ነገሥታቶችዋ አለቆችዋም ሁሉ በዚያ አሉ፤ ኃይል የነበራችው በሰይፍ ከተገደሉት፥ ካልተገረዙት እና ወደ ጉድጓድ ከሚወርዱ ጋር ተኝተዋል።
ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ያሳድዱአትና ይበዘብዙአት ዘንድ በልባቸው ሁሉ ደስታና በነፍሳቸው ንቀት ምድሬን ርስት አድርገው ለራሳቸው በሰጡ በቀሩት አሕዛብና በኤዶምያስ ሁሉ ላይ በቅንዓቴ እሳት ተናግሬአለሁ፤
የአብድዩ ራእይ። ጌታ አምላክ ስለ ኤዶምያስ እንዲህ ይላል፦ ከጌታ መልእክት ሰምተናል፥ መልእክተኛ ወደ አሕዛብ ተልኮ፦ ተነሡ፥ በላይዋም በጦርነት እንነሣ ብሏል።